fbpx

ቀዳማዊት እመቤት በተለያዩ ክልሎች ለሚገነቡ ትምህርት ቤቶች የግንባታ የማስጀመሪያ ስምምነት ፈረሙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ለሚገነቡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግንባታ ማስጀመሪያ ስምምነት ፈረሙ።

ቀዳማዊት እመቤቷ የግንባታ ማስጀመሪያ የመግባቢያ ስምምነቱን ከክልሎቹ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በትናንትናው ዕለት መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡

የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ የሚከናወነው በደቡብ ክልል ሸካ፣ጌዲዮና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ አድሀ ሊበን ወረዳና በጉጂ ዞን ነው ተብሏል።

የትምህርት ተቋማት ግንባታ የሚከናወንባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እጥረት ውስጥ ነበሩ መሆኑ ተነግሮዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤቷ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ባለሃብቶች ትምህርት ቤቶች ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች የትምህርት ተቋማትነ በመገንባት የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ የስራ ኃላፊዎች የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ስራ መግባት እንዲቻል ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር እሸቱ ከበደና የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በክልሎቹ ያለውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እጥረት የሚያቃልል መሆኑንም ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተገንብተው ወደ ስራ እንዲገቡ የአካባቢው ህብረተሰብ በማስተባበር እንደሚሰሩም ኃላፊው ቃል ገብተዋል።

ምንጭ፦ኢዜአ

Share.

About Author

Leave A Reply