Tuesday, September 25

በሞያሌ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ በህይወት እና በአካል ላይ ጉዳት ደረሰ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሞያሌ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እንደነገሩን ከሆነ በሞያሌ ከተማ መናሃሪያ አካባቢ በኦሮሞ እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል ግጭት ከተከሰ በኋላ የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ቢያንስ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ለጉዳት ተዳርገዋል።

የሞያሌ ወረዳ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት ምክት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሁሩካ ጎዳና ለቢቢሲ እንደተናገሩት በፍንዳታው ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና ወደ 63 የሚጠጉ ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ከሳምንታት በፊት በሞያሌ ከተማ በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች በስህተት ተፈጸመ በተባለ ግድያ 10 ሰዎች ተገድለው በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ ለደህንነታችን ያሰጋናል በማለት ድንበር ጥለው መሸሻቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦BBC

 

Share.

About Author

Leave A Reply

ፈጣን ዜናዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ያግኙ

Kaliti Press - The Fastest

JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLOSE