በአርባምንጭ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአርባምንጭ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ መያዙን የጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደተናገሩት፥ ከትናንት በስቲያ ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች ጋር የተገኘው ተቀጣጣይ ፈንጂም ዓይነቱን ለመለየት ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

ከዚህም ሌላ በአንድ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ተጭኖ የገባ አነስተኛና ዘመናዊ የጦር መሣሪያ፣ ከ150 በላይ ስለቶች፣ የባንክ ቼኮችና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦችም እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

መሳሪያዎቹንና ገንዘቦቹን ሲያዘዋወሩ የተገኙ ግለሰቦች ከነተሽከርካሪዎቹ ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው እንደሚገኝ ኮማንደር ረታ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

 

Share.

About Author

Leave A Reply

ፈጣን ዜናዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ያግኙ

Kaliti Press - The Fastest

JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLOSE