fbpx

በአንበሶች ጊቢ የሚጠበቁ አንበሶች በርካቶቹ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአዲስ አበባ አንበሳ ጊቢ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አንበሶች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደ ገለጹት ከዚህ ቀደም የአንበሶቹን ድምጾች በብዛት የሚሰሙ ሲሆን ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ግን ምንም ድምጽ እንደማይሰሙ ነው የተናገሩት።

ምንም እንኳ የድርጂቱ ሀላፊ አንበሶቹም ሆነ የሌሎቹ እንስሳት ጤና በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛል ቢሉም ነዋሪዎቹ ግን በዚህ አይስማሙም።

አንበሶቹ ከእንክብካቤ ብዛት የተነሳ መሞታቸውን እና ለእንስሳቱ የሚገዛው ስጋም በህገ ወጥ መንገድ እንደሚሸጥ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ አንበሶች ጊቢ በእድሳት በሚል ሰበብ ከአራት አመት በላይ ተዘግቶ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply

ፈጣን ዜናዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ያግኙ

Kaliti Press - The Fastest

JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLOSE