ብአዴን አመራር አምላኪ ድርጅት አይደለም!” የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ማዕከላዊ ኮሚቴው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ረጅም ጊዜ በመውሰድ በዝርዝር የተመለከታቸው ሃገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተፈፃሚ እንደሚሆኑ አብራርተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ ከተናገሩት ጭብጦች መካከል፡-

“ለውጥ መጀመር በራሱ ጥሩ እርምጃ ነው፤ ለውጥን ማስቀጠል ግን ትልቅ ፈተና ነው!”

” . . . ወጣቱ የሚፈለገው ወፍራም ማብራሪያ ሳይሆን ተጨባጭ ምላሽ ነው!”

“ብአዴን አመራር አምላኪ ድርጅት አይደለም፤ አመራሩ ለእርምት ባለው ዝግጁነት ለበለጠ ተጠያቂነት እና ለበለጠ ኃላፊነት ስምሪት የሚሰጥ ድርጅት እንጂ!”

“ህዝባችን ውስጥ ያለውን ብርቱ የለውጥ ፍላጎት እና ጠንካራ የለውጥ አቅም በሚገባ አስተባብሮ ለመጠቀም ዳር እስከ ዳር መንቀሳቀስ ይጠይቀናል!”

“በችግር ውስጥ ተሰብስቦ ችግርን እየሞቁ መሰንበት ዘመኑ አይፈቅድም፤ ለጀመርነው የለውጥ ጉዞም በእጅጉ አይመጥንም፤ ስለዚህ በሃገርና በክልል ጉዳይ የተለያየ ሃሰብ ቢኖረንም በጋራ መስራት የሚከለክለን አንዳች ነገር አይኖርም!”

“ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን አጀንዳ የበለፀገ ሃገር እና ክልል መገንባት ነው!”

“በእጃችን ያለውን ስኬት አሳንሰን ልናይ አይገባም፤ ሃገራችንም ክልላችንም በለውጥ ጉዞ ላይ ናቸው፤ ቁምነገሩ ይህንን ሰፊ ለውጥ የሚመጥን አመራር መስጠትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በባለቤትነትነት መንፈስ ማሰማራት ነው!”

የመገለጫው ሙሉ መረጃ አደደረሰነ የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

 

Share.

About Author

Leave A Reply