ኢህአዴግ በኦሮሚያ የአደራ መንግስት ለመመስረት ሳያስብ አልቀረም

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ግርማ ካሳ

በአዲስ አበባ ዙሪያ  ከግተኛ ተቃውሞ ተደርጓል። የተመድና የአፍሪካ ሕብረት ሰራተኞች ባሉበት እንዲቆዩ ታዘዋል ። በሱሉልታ ፣ በለገጣፎ ፣ በቡልቡላ ፣ በጎሮ፣ በሰበታ በአለም ገና፣ በቡራዮ ተቃዉሞዎች የተደረጉ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ውስጥ በአየር ጤና ተቃዉሞዎች እንደነበሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ጨመሮ በበርካታ የኦሮሚያ ግዛቶች ተቃዉሞዎች ለሁለተኛ ጊዜ የተደረጉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት ሲደረጉ ከነበሩ ተቃዉሞዎች ጋር ሲነጻጸር ተቃዉሞዎቹ ከሞላ ጎደል በሰላም ነው የተጠናቀቁት።

የሕዝብን ጥያቂ ከሕዝብ ጋር ሆነው በተጠና መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን እንደሚሰሩ የገለጹት የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር፣ ዶር አብይ አህመድ፣ አድማው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ዛሬ ለተፈቱትን፣ ነገ ለሚፈቱትን እስረኞች አቀባበል ለማድረግ፣ እነ አቶ ለማም ከሕዝብ ጋር ሆነው ለዉጥ እንዲመጣ የጀመሪትን የበለጠ እንዲገፉበት ጊዜም ለመስጠት፣ ሰልፊ ቢቆም የሚመርጡ ጥቂቶች አይደሉም።

ሆኖም ተቃዉሞው የመቀነስ ሳይሆን የመጋል አዝማሚያ እያሳየ ነው። በተለይም ዛሬ በአዲስ አበባ ዙሪያ የታየው ወደ መሐል ከተሸጋገረ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ያን ተከትሎ የወያኔ መንግስት ሊፈርስ ይችላል፣ በአንጻሩም ደግሞ ወያኔ አጋዚን በስፋት በማሰማራት ከፍተኛ ደም መፋሰስ ሊከሰት ይቻላል።

እርግጥ ነው ፣ እስከ አሁን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አጋዚ እንዳይገባ ያከላከል ነበር። እነ ለማ ያወቃሉ አጋዚ ካለ ደም እንደሚፈስ። የሕዥብ ደም እንዳይፈስ ትልቅ ጥንቃቄ ነው እያደረጉ ያሉት። ሆኖም ሕወሃቶችም ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ተቃዉሞው እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው አንዳንድ ተንታኞች ይናገራሉ። ለሕወሃት ትልቅ ራስ ምታት የሆኑበት የአቶ ለማ ቡድን እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። አቶ ገዱን ለማንሳት በአሁኑ ወቅት ሕወሃት በባህር ዳር እነ በረከትን አሰማርቶ፣ በብአዴን ውስጥ እየተንቀሳቀስ ሲሆን፣ በኦህዴድ ውስጥ የነበሩት አሽከሮቹ በብዛት ስለተወገዱ (ከወርቅነህ ገበየሁና ጥቂት መሰሎቹ በስተቀር) ግን እነ አቶ ለማን ለማንሳት አልቻለም።

ስለዚህ አንዱ ስትራተጂያቸው የለማ ቡድንን ማዳከምና አቅም የሌለው እንደሆነ ማሳየት ነው። የለማ ቡድን ህግና ስርዓት ማስጠበቅ አቅቶት እንዲፍረከረክ ፍላጎት አላቸው። ከዳር ሆነው እየጠበቁ ያሉቱም ይሄን ሳይሆን አይቀርም። እነ ለማ ነገሮችን ማረጋጋት ካልቻሉ፣ በኦሮሚያ ወታደራዊ አገዛዝ ሊዘረጉም ይችላሉ። ተስፋ ኪሮስ ሳህሌ የተባለ፣ አፍቃሪ ሕወሃት ጦማሪ ፣ “ኦህዴድ ክልሉን ማስተዳደር ካቃተው ደግሞ እስከሚቀጥለው ምርጫ በባላደራ መንግስት እንዲተዳደር ማድረግ እንደ ኣማራጭ ሊታይ ይችላል” ሲል የጦምረውን በማየት የሕወሃት ስትራቲጂ ምን እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ “የክልሉ መንግስት ምንም ማድረግ አልቻለም። ነገሮችን ለማሻሻል እየሞከርን ነው። በአገር ውስጥ ግን አናርኪ መፈጠር ስለሌለበት የወሰድነው እርምጃ ወስደናል” ቢሉ ለምን የሚላቸው አይኖርም። ~ ቃሊቲ ፕሬስ

Share.

About Author

Leave A Reply