የመንግስታቱ ድርጂት የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ጥረት የኤርትራን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሊያሻሽል እንደሚችል ገለጸ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ የሰብዓዊ መብት መርማሪ የኤርትራን የሰብዓዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ በጄኔቭ ሲዊዘርላንድ ባሳለፍነው ሳምንት ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ሪፖርት አቅርቦ ነበር፡፡

በሪፖርቱም በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሁንም እንዳለ ምርመራውን የመሩት ሼላ ኪዛሩዝ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና በኢትዮጵያና በኤርትራ ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የተደረገው የሰላም ጥረት መልካም ጅምር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ በመጠቀም የሀገሪቱ ዜጎች በውዴታ ሳይሆን በግዴታ በውትድርና ግዳጅ ውስጥ እንዲገቡ ታደርጋለች ብሏል ሪፖርቱ፡፡

ኢትዮጵያ የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ለማሻሻል የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምትቀበል ማስታወቋን ተከትሎ ሰሞኑን የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ኢትዮጵያ በመምጣት ውይይትና ጉብኝት ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply