የአዲስ አበባ ከተማ ልማት ቢሮ መሐንዲስ በሙስና በወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ መሐንዲስ፣ በሕገወጥ መንገድ መሬት በመውሰድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡

ተጠርጣሪው አቶ እስክንድር ዳሪ በከተማ ልማት ቢሮ መሐንዲስ ሆነው ሲሠሩ፣ የተለያዩ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዶችንና የምስክር ወረቀቶችን በመውሰድ በባለቤታቻው፣ በቤተሰቦቻቸውና በሌሎች ግለሰቦች ስም ሐሰተኛ ሰነዶችን ማዘጋጀታቸውን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪው ያዘጋጁትን ሐሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች፣ የሊዝ ውል፣ ሪከርድና ማኅደር በማዘጋጀት 175 ካሬ ሜትር ቦታ መውሰዳቸውንም አክሏል፡፡ ቦታውን የወሰዱት በቀድሞ ወረዳ 28 ቀበሌ 04 ወይም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

አቶ እስክንድር ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በጥቅም በመተሳሰር የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት መውሰዳቸውን መርማሪው ገልጸው፣ ተጠርጣሪው ከባድና ውስብስብ የሙስና ወንጀል በመፈጸማቸው፣ እንዲሁም በመንግሥት ላይ ያደረሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(2) መሠረት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ~ ሪፖርተር

Share.

About Author

Leave A Reply