የወልዲያ ስቴዲየም ወደ እስር ቤትነት መቀየሩን ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የብአዴንን መግለጫ አነበብኩት። መግለጫው ከአንድ ታዛዥ የሚጠበቅ ነው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው ባለፈው ሕዝብ እናረጋጋለን ብለው ችግሩ የአመራሩ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናግረው ነበር።

ሆኖም አቶ ገዱ ወደ ባህርዳር እንዲመለስ ተደርጎ አለምነው መኮነን ወደ ወሎ ተላከ። አለምነው ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር መግባባት አቅቶት የመራው ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ህዝብ በተደጋጋሚ ጥሎት ወጣ። አለምነው ሕዝብን አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ ከአዳራሽ ውጭ የነበሩ ወጣቶችን በአጋዚ ሲያስር እና ሲደበድብ ሰንብቷል።

አቶ አለምነው መኮንን ተልኮ መሄዱን ሽማግሌዎቹ ይፈቱ ያሏቸውን እስረኞች “ለምርመራ ይፈለጋሉ” በማለት አረጋግጧል። የመርሳ ከተማ ከንቲባ “ጉዳዩን ፌደራል ይዞታል” ብሏል። ከአለምነው ውጭ የብአዴን አመራሮች እና ኮማንደር አማረ ሕዝብም ማነጋገር አልደፈሩም። የታዘዙትን ይዘው ሕዝብ ፊት መሄድ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታል።

የታሰሩትን በሽማግሌዎች ጥረት መፍታት ተጀምሮ የነበር ቢሆንም ባለፉት ሁለት ቀናት ወጣቶች እንደገና በጅምላ እየታፈሱ ነው። የወልዲያ ስቴዲየም ወደ እስር ቤትነት መቀየሩን ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው። ቀሪዎች የት እንደገቡ አልታወቀም። የብአዴን መግለጫ ባለፈው እነ ገዱ ሕዝብን ካሞኙበት ድስኩር ተቃራኒ ነው። ችግሩ የእኛ ነው ካሉ በኋላ በአለቆቻቸው ትዕዛዝ ንፁሃንን እያሳፈሱ ነው!

መግለጫው የገደሉና ያወደሙ እንደሚጠይቁ ያትታል። ሆኖም አንድም የአጋዚ አልሞ ተኳሽ እንደማይጠየቅ ግልፅ ነው። መግለጫው የወጣው የትህነግ ንብረትን አቃጥለዋል፣ ዳኛውን ገድለዋል ለተባሉት ወጣቶች ብቻ ነው። በዚህ ሰበብ ገዥዎቹ የሚጠሉትን ሕዝብ ለማሰቃየት ጊዜ እና ሰበብ አግኝቷል፣ ብአዴንን የመሰለ መሳርያ፣ ታዛዥ አግኝተዋል!

 

ጌታቸው ሽፈራው

Share.

About Author

Leave A Reply