Monday, September 24

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስልጣን ለቀቁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በበርካታ የሙስና ወንጀሎች ክስ የሚቀርብባቸው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ይፋ አደረጉ። የ75 አመቱ ጃኮብ ዙማ ስልጣናቸውን በአስቸኳይ ለምክትላቸው እንዲያስተላልፉ ፓርቲያቸው ኢ.ኤን.ሲ በወሰነባቸው አስገዳጅ ውሳኔ ሳቢያ ነው ስልጣን ሊለቁ የቻሉት።

እ.ኤ.አ. በ2009 ወደ ስልጣን የመጡት ዙማ ከሀያ በላይ የሙስና ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው በሀገሪቱ ውስጥ የአንድ ጎሳ የበላይነት እንዲሰራፋ አድርገዋል በሚል በተለያዩ ጊዜያት ሲወነጀሉ ቆይተዋል።

በእነዚህና በርካታ ምክኒያቶች ተቃዋሚዎቻቸው በፓርላማ ውስጥ ቀርበው ንግግር እንዳያደርጉ ሲያወግዟቸው እና ሲቃወሟቸው የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ቢነሱም በፓርቲያቸው ውስጥ አሁንም ቁልፍ ስፍራ ይዘው ይቀጥላሉ ተብሏል። ~ ቃሊቲ ፕሬስ

 

Share.

About Author

Leave A Reply

ፈጣን ዜናዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ያግኙ

Kaliti Press - The Fastest

JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLOSE