ግብፅ በአገሯ የታሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደምትፈታና በሊቢያ በአሸባሪዎች የተገደሉ ኢትዮጵያዊያን አፅም ወደ አገራቸው እንዲመለስ እገዛ እንደምታደርግ አስታወቀች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ ካይሮ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የነበረን ጥርጣርሬ በማስወገድ በመተማመን ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ።

ከውይይቱ በኋላ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ መግለጫውን በአማረኛ ቋንቋ ሰጥተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸውም፤ ግብጽ በሀገሪቱ ታስረው የነበሩ ኢትዮጵውያን እንዲፈቱ መስማማቷ ተገልፆል።

ከአመታት በፊት በሊቢያ በአሸባሪዎች የተገደሉ ዜጎች አፅም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በክብር እንዲያርፍ ግብጽ እገዛ እንደምታደርግም መግባባት ላይ ተደርሷል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply