ፌስቡክ የቢትኮይንና ሌሎች የኢንተርኔት መገበያያ ገንዘብ ማስታወቂያዎችን አገደ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ፌስቡክ ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች የኢንተርኔት መገበያያ ገንዘብ ማስታወቂያዎችን ማገዱን አስታውቋል።

ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ፌስቡክ እንዳስታወቀው፥ ኢንተርኔት መገበያያ ገንዘብ ማስታወቂያዎች ደንበኞችን ወዳልተፈለገ መስመር የሚያስገቡ መሆኑን ተከትሎ ነው የታገዱት።

እንደ ቢትኮይን ያሉ ኢንተርኔት መገበያያ ገንዘቦች መበራከታቸውን ተከትሎም በዓለም ገበያ ላይ ከፍተኛ ማጭበርበሮች እየተስተዋሉ መጥተዋል።

የፌስቡክ የምርት አስተዳደር ዳይሬክተር ሮብ ሬትለን በብሎግ ፖስት ገፅ እንዳስታወቁት፥ ኩባንያው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች የኢንተርኔት መገበያያ ገንዘቦች ማስታወቂያ ማስተላለፍ አቁሟል።

የኢንተርኔት መገበያያ ገንዘቦች ማስታወቂያ ፌስቡክ ላይ መሰራጨት ዳግም እንዲጀመር ለማድረግ የፖሊሲ ማስተካከያ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

“ሰዎች በፌስቡክ አማካኝነት ስለ አዳዲስ ምርቶች እና አገልግሎቶች ያለ ምንም ፍራቻ እና ጥርጣሬ እንዲማሩ እንፈልጋለን” ሲሉም ዳይሬክተሩ ፅፈዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply