የተከበራችሁ የቃሊቲ ፕሬስ ተከታዮች። እንደምን ሰነበታችሁ። ሰሞኑን መንግስት በዝቅተኛው የንግድ ማህበረሰብ  ላይ በጣለው ከፍተኛ የግብር ክፍያ ግመታ ሳቢያ አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የንግድ ድርጅቶች ተዘግተዋል። “የምናገኘውና ለግብር ክፍያ የተጠየቅነው ፈጽሞ አይመጣጠንም” ያሉት ነጋዴዎች ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥትተዳደር ቆይታለች። ምንም እንኳ የአዋጁ ማብቅያ ጊዜ ገና አስራአምስት ቀናት ያህል ቢቀሩትም በተቃውሞ መንገዶች ተዘግተዋል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል ተቃውሞው ዳግም አገርሽቷል። በእነዚህ እውነታዎች ላይ ተንተርሰን አቶ ጃዋር መሀመድን ለቃለ መጠይቅ ጋብዘናል። ያድምጡን። www.kalitipress.com

Related Videos

Opinion

Follow us on Facebook

Polls

Nothing found!