ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የክብር ዶክትሬት ሰጠ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለጋዜጠኛ መሃመድ አህመድ (መሃመድ ቆጴ) የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡

ዩንቨርስቲው በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ 8152 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በዚህ የመረቃ ዝግጅትም ዩንቨርስቲው ለርዕሰ መስተዳድር ገዱ እንዳርጋቸውና የመጀመሪያው የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ሆነው በሃረር ለሰሩት መሃመድ አህመድ (መሃመድ ቆጴ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ከዚህ በፊት ዩኒቨርስቲው በማሽላ ላይ ተመራማሪ እና የምግብ እና የእርሻ ድርጅት አማካሪው ለሆኑት ለፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ እና ለጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ብቻ እንደሰጠ ተገልጿል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply