ሀገር አቀፍ የተማሪ ወላጅ ህብረት ተመሰረተ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሀገር አቀፍ የተማሪ ወላጅ ህብረት መመስረቱ ተገልጿል።

ህብረቱ ከሁሉም ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ሲሆን፥ በአዳማ ከተማ በዛሬው እለት መመስረቱ ነው የተገለጸው።

ህብረቱ በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስት ዴኤታ የሚመራ ሆኖ እያንዳንዱን ክልል የሚወክሉ 11 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች እንዳሉትም ተነግሯል።

በህብረቱ ምስርታም ኢንጂነር ጌታቸው ስመኝን ከአዲስ አበባ ሊቀመምበር ፣ ወ/ሮ መሰረት ተክሌ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ሊቀመምበር እና አቶ ሁሴን በዳሶን ከኦሮሚያ ክልል ጸሀሃፊ ሆነው ተመርጠዋል።

የህብረቱ ዋና ዓላማ የተማሪ ወላጆች በተዋረድ ከመንግስት ጋር የሚገናኙበት መዋቅር በመዘርጋት የትምህርት ጥራት መረጋገጥ ላይ በጋራ ለመስራት ሲሆን፥ ምክር ቤት እንደሚኖረውም ነው የተገለጸው።

ህብረቱን የሚመሩት የትምህርት ሚንስትር ዴኤታው አቶ መሃመድ አህመድ ህብረቱ ወላጆች ሁለንተናዊ ሰዕብናው የተሟላ ዜጋን በመፍጠር ረገድ ያላቸውን በጎ ሚና እንዲያበረክቱ ብሎም በወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራር አካላት መካከል ጤናማ እና ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በትናንትናው ዕለት በአዳማ ከተማ የተጀመረው እና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና የሚዲያ አካላት ያሳተፈው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ግብዓት ማሰባበሰቢያ ሀገር አቀፍ የተማሪ ወላጅ ህብረትን በማቋቋም ተጠናቋል።

Share.

About Author

Leave A Reply