“ሀገር ያወረሱንን አባቶች አደራ ተረካቢ ትውልድ መፍጠር አለብን” አቢይ አህመድ በኬኒያ ለተማሪዎች የተናገሩት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት በኬኒያ ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና በፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ ኬኒያታ ልዩ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ተማሪዎች ንግግር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው “በአሁን ወቅት ሀገር ሰርተው ያስረከቧቸውን አባቶቻቸውን ህልም የሚያሳኩ መሪዎች እጥረት እያጋጠማት ነው።” ብለዋል።

“ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ ወጣቱን ትውልድ በአባቶች መሰረት ላይ ማነጽና ሀላፊነቱን የሚወጣ አድርጎ ማስተማር ይገባል” በማለት ወጣቶች የነገዋ ሀገራቸው ተረካቢዎች ለመሆን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ መክረዋል።

ኬኪኒያ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡት 54 ተማሪዎች በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያመጡና የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በቅርበት የሚከታተሏቸው ተማሪዎች ሲሆኑ በወቅቱም የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አቅርበዋል። ~ ቃሊቲ ፕሬስ

Share.

About Author

Leave A Reply