ሁሉም ዜጋ በአንድ ኢትዮጵያ እንዲኮራ ነው የምፈልገው – አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በፋና ራዲዮ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ፋና:- አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አጼ ሀይለስላሴን እንዴት ይገልጿቸዋል?
አቶ ቡልቻ:- በእርሳቸው ጊዜ ሰው በጣም ይከባበር ነበር። እንደምታውቂው እኔ ኦሮሞ ነኝ። እሳቸው ይሄ ነገር አንድም ጊዜ ትዝ ብሏቸው አያውቅም።
ፋና:- በአንድ ወቅት የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ነበር።
አቶ ቡልቻ:- እኔ ኦነግን አከብራለሁ። ይሁን እንጂ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ እገነጥላለሁ የሚለውን ነገር አልቀበለውም። ገንጥሎ የት ይወስደዋል?
ፋና:- በቀጣይ ምርጫ ምን አስበዋል?
አቶ ቡልቻ:- ከፎቅ ወድቄ በህክምና ነው ያሳለፍኩት። አሁን እያገገምኩ ነው። እና የግል ተወዳዳሪ ሆኜ ፓርላማ ለመግባት እዘጋጃለሁ።
ፋና:- ምን ማስተላለፍ ይፈልጋሉ?
አቶ ቡልቻ:- አንድ ኢትዮጵያ! ልክ እንደ እንግሊዝ። ኢንግሊዞች እንግሊዛዊ ነኝ ማለት ይወዳሉ። ልክ እንደዝያ ሁሉም በኢትዮጵያዊነቱ እንዲኮራ ነው የምፈልገው።
(ዛሬ ማምሻውን በፋና 120 ደቂቃ ዜና ዘገባ )
አቶ ቡልቻ የ88 አመት እድሜ ባለጸጋ ሲሆኑ የመጀመርያው የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ሲሆኑ የመጀመርያው የግል ባንክም መስራች ናቸው።

 

Share.

About Author

Leave A Reply