ህወሀትና አረና የሀውዜንን ፖለቲካ እየተጫወቱ ነው – ሚኪ አማራ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ባለፈዉ ወቅት የአማራ ትምህርት ቤቶችን ሁኔታ በዘመቻ መልክ ግልጥልጥ አድርገን አሳይተን ብዙ ህዝብ የተቆጨበት ነበር፡፡ አማራ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁኔታዉን በማየት በጣም አዝኗል፡፡

ብአዴንም በድንጋጤ ክዉ ብሎ ማእከላዊ ኮሚቴ ላይ አጀንዳ አድርጎት ነበር፡፡ በዚህ ማህል ግን አንዳንድ ወገኖቻችን ትምህርት ቤት መስራት ወይም የአማራን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ማሻሻል ትግሉን ይጎዳል ፤ኑሮዉ ከተሻሻለ አይታገልም አይነት ከሰማይ ይሁን ከመሬት የመጣበት የማይታወቅ theory ይዘዉ ብቅ ብለዉ ነበር፡፡ ይህ አካሄድ የ Hawzen politics syndrome (የሃዉዜን ፖለቲካ) ይባላል ወይም ብየዋለዉ፡፡

የሃዉዜን ፖለቲክስ ማለት ህዝቡ ለትግል እንዲነሳሳ ህዝቡ ላይ ደባ እልቂት መፈጸም ማለት ነዉ፡፡ የትግራይን ህዝብ ለትግል ለማነሳሳት ህወሃት የሃዉዜንን ህዝብ ዛሬ ገቢያ እንዳትቀሩ ስብሰባ አለ ብላ ሁሉም ሰዉ ወደ ገቢያ ይመጣል፡፡

በጎን ስብሰባ ገቢያ ላይ ሊያደርጉ ነዉ የሚል መረጃ ለደርግ መረጃ ህወሃቶች ይልካሉ፡፡ ደርግ የሚባል ጅል ደግሞ ይሄን ይሰማ እና ገቢያ ላይ ቦምብ ያዘንባል፡፡ ህወሃቶች ከገቢያዉ ማዶ ሁነዉ ይሄን ነገር በቪዲዮ ይቀርፁ ነበር፡፡ እና ህዝቡን ለትግል ለማነሳሳት ተብሎ ብሀዝቡ ላይ የሚፈጸም ሴራ አጠቃላይ “Hawuzen politics” ይባላል፡፡

በነገራችን ላይ በለሳ ሃሙሲት ላይ፤ ሰቆጣ ላይ ይሄን ነገር አስደርገዋል፡፡ በቪዲዮ ግን አልቀረጹትም ለታሪክ እንዲኖር ስለማይፈለግ፡፡ ህወሃት እና አረና አሁን እራሱ የሚጫወቱት “የሃዉዜን ፖለቲክስ” ነዉ፡፡ የትግራይ ተወላጅ ላይ በየትኛዉም ሀገር ጥቃት አንዲፈጸምበት ሲጸልዩ ነዉ የሚያድሩት፡፡ ምክንያቱም የሚከሰተዉ ጥቃት የትግራይ ህዝብ የጠነባዉን የህወሃትና አረናን ፖለቲካ ደጋፊ ያደርገጋለል ብለዉ ነዉ፡፡

ወደ እኛ ስመጣ የትምህርት ዘመን እየደረሰ ነዉ፡፡ መስከረም መቷል፡፡ መስከረም ላይ ደብተር እና ዩኒፎርም መግዣ ስላጣ ብቻ ትምህርት ቤት የማይሄድ ብዙ ሚሊየን ህጻናት አሉ፡፡ መስከረም ላይ ደግሞ የሚሸጥ እና የሚለወጥ ነገር አይደርስም በተለይ ለገበሬዉ፡፡ ስለዚህም ሃዉዜን ፖለቲክስ መጫወታችን ትተን እያንዳንዳችን ለጎረቤት ልጅ ደብተር በመግዛት መተባበር አለብን፡፡ የሚችል ትምህርት ቤት በመገንባት፤ በመጠገን፤ ለላይበራሪ መጽሃፍ በመስጠት እና የመሳሰሉት፡፡

በእዉቀት፤ በቴክኖሎጅ፤ እና በኢኮኖሚ የጠነከረ ህብረተሰብ እንኳን አንድን አካባቢ አይደለም አለምን ይለዉጣል፡፡ To make our people free, we just don’t need to play Houwzen politics but to improve the social, economic and political situations of our community.

Share.

About Author

Leave A Reply