ህወሀት ከእንግዲህ የማያንሰራራ ያበቃለት ቡድን ነው ሲሉ ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ህወሀት ከእንግዲህ የማያንሰራራ ያበቃለት ቡድን ነው ሲሉ ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ። የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ መንግስት
ከእንግዲህ በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት በቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።

“አዲስአበባ ድረስ ታንክና መድፍ ይዘን የገባነው ለሁለቱ ህዝቦች ዘላቂ ጥቅም ስንል ነበር” ሲሉም ተደምጠዋል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት በኤርትራ ቴሌቪዥን በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በህወሃት አደፍራሽነት 25 አመታት የገጠማቸውን ኪሳራ የሚያስመልሱበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነም ነው የተናገሩት።

 

Share.

About Author

Leave A Reply