Thursday, January 17

“ህዝበኝነት” Populism ማንን ሊያሰጋ ይችላል?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቲም ለማ የህዝብን ጥያቄ ጥያቄው አድርጎ፡ መሪ አልባ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት መሪ ሆኖ ጥያቄና ፍላጎት በተገቢው መንገድ እየመለሰና እያስመለሰ ወደ ስኬት መምጣት የጀመረ ሰሞን “ህዝበኝነት” Populism በነሱ አጠራር cheap populism እንደመምቻ ሲጠቀሙበት ነበር።

“ህዝበኝነት” Populism “Ism” እንደ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝም፣ ኮሚኒዝም ወይም ኢምፔሪያሊዝም… አመለካከቶችንና መርህን የሚያንፀባርቅ ቅጥያ የተለያዩ ርእዮተዓለሞች መልክ ይዘው የሚጠሩበት እንደሆነ እንረዳለን። የህዝበኝነት Populism መጀመሪያውም መጨረሻውም “ህዝብ ትክክል ነው” ነው። በርግጥ ሊብራል በሆነ የፖለቲካል ስርዓት ላይ ህዝበኝነት “ሁሉም የራሱን መንገድ መከተል ይችላል፣ እኔ በራሴ ትክክል ነኝ” የሚለውን ወጣ ያለ ትርጉም ይይዛል።

ዶናልድ ትራምፕን ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ያበቃው ሕዝበኝነት ነው። ትራምፕ ህዝቡን ለመቀስቀስና ለመመረጥ የተጠቀሙት የ”ሪፓብሊካኖቹን” ርእዮተዓለም ሳይሆን ህዝቡ የሚፈልገውን ነገር ነው። “ህገወጥ ነዋሪውን አባርራለሁ፣ ጫና እቀንሳለሁ” አለና ህዝቡን አስከተለ ምርጫውን አሸነፈ።

እኛም ሃገር የሆነው ይህ ነው። ህዝቡ ያለፉት 27 ዓመታት ከዛም በፊት በነበሩት 17 ዓመታት እርሱ በማይፈልገውና ባልመረጠው ፍላጎቱንም ፈጽሞ ሊያሳካለት ባልቻለ ፡ሊችልም በማይችል “የማውቅልህ እኔ ነኝ” በሚል አምባገነናዊ ስርአት ተተብትቦ ፡ መተንፈሻ አጥቶ ሲሰቃይ ነው የኖረው።

ከ1997ቱ በኋላ ተዳክሞ የነበረው የህዝብ ለውጥን የመፈለገ እንቅስቃሴ ዳግም ከ ሁለት ዓመት በፊት እንደ አዲስ ሲቀሰቀስ፡ ያንን የለው ፍላጎት ከህዝብ ጎን ቆሞ ኪፊት ሆኖም የሚመራ የተደራጀ ሃይል አልነበረም። ተቃውሞ ይነሳበት የነበረው አካል(OPDO& ANDM) ለውጥ ፈላጊ ተራማጅ ሆኖ ቀረበ ፡ በተለይ OPDO ለማ መገርሳና ቲሙ ወደስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ህዝበኝነትን ተላብሰው ለውጡን shape አድርገውታል።

ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣበት ዕለት አንስቶ ይህንን አስተሳሰብ ተላብሶ ከህዝቡ ቀድሞ የህዝቡን ጥያቄ እየመለሰ አብዮታዊ ምናምን ከሚባል ትብታብ እየፈታን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ህዝብ በፈለገው ሳይሆን እኛ በፈለግንለት ባሰመርንለት መስመር ብቻ ነው መጓዝ አለበት ለሚሉ በድኖች ቅዠት ሆኖባቸዋል። ለዛም ነው 27 ዓመት የስርአቱ ዋስጠበቃ የነበሩ ኮካዎች ተቃዋሚ፤ ተቃዋሚው ደግሞ ደጋፊ ሆኖ ብቅ ያለው።

አምባገነኖች የህዝብን መነሳሳትና ለውጥ ፍለጋ ለማሰናከል ሲፈልጉ፣ ህዝቡን ጠይቀው ሳይሆን የሚያዋጣህ “ህዝባዊነት” ነው በሚል ወደሚፈልጉት መስመር ለመቀልበስ ወይም ለመጠምዘዝ፣ ብሎም መራጭ ሊሆን የተገባውን ህዝብ በሚፈልጉት ቦይ እንዲፈስ በማስገደድ ስራ ይጠመዳሉ። ለዚህም በህዝበኝነት እንቅስቃሴ በግብታዊነት የሚወሰዱትን አንዳንድ ጥፋቶችና የሚያስከትሉትን ችግሮች እንደማስረጃ በመጠቀም ለውጡን ቀልብሰው ዳግሞ ጭቆናቸውን ይቀጥላሉ። የህወሃትና የደጋፊዎቿ የሰሞኑ መንደፋደፍ ለዚህ ማሳያ ነው። በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተቀናጀና በተጠናበት መልኩ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት የመለያየት(እዚህ ላይ ቀድሞ ኮሽታ የማይሰማባቸው አካባቢዎን ጭምር)እንደመሳሪያ በመጠቀም ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ ። ይህም እንደ ሃገር በጠ/ሚ ዐብይ እየመጣ ያለውን ለውጥ ከስሩ ለመቅጨት እየተደረገ ያለ ሴራ መሆኑን ለመናገር የፖለቲካ ተንታኝ መሆን አይጠበቅም።

ታዲያ ይሄ “ህዝበኝነት” Populism ማንን ሊያሰጋ ይችላል?The Economist ላይ የፖለቲካው ምሁር እንዳስቀመጡት “populism’s belief that the people are always right is bad news for two elements of liberal democracy: the rights of minorities and the rule of law.”

ወደ እኛ ሃገር context ስናመጣው ህውሃትና ደጋፊዎቹ የፈሩለት አላማ ከክፋትና ከልውጥ ቀልባሽነት ያለፈ ምንም አይታይም። በፖለቲሺያን የተፈራለት የአናሳዎችንን መብት አለማክበርና የህግ የበላይነት እንዳይሰፍን ያደርጋል ስጋት በህውሃት ቀድሞ የተካዱ እንደ ስርአትም ያልነበሩን elements ናቸው።

  1. የህግ የበላይነት አልነበረም፤

2.እንደ ህወሃት “አናሳ ብሄር(ልንለው እንችላለን)የለም ሁሉም ከ 50% በታች ነው ስለዚህም ሁሉም minorities ነው” አቋም ሆኖ የነበር።

(አብረሀም ሲሳይ)

Share.

About Author

Leave A Reply