ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ኃይል የከተማ አስተዳደሩ አይታገስም – ኢ/ር ታከለ ኡማ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የነገው የየኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አቀባበል ካለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ምክትል ከንቲባው ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

በተጨማሪም ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን፣ ከጸጥታና ደህንነት፣ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ጋር ሰፊ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በኤርትራ የሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር በነገው ዕለት መስከረም አምስት 2011 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በውጭ ሀገር ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በርካታ ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply