ለላሊበላ ቅርስ ጥገና የሚውል 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለላሊበላ ውቅር ዓብያተ ክርስቲያናት ጥገና አገልግሎት የሚውል 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ልዑል ዮሃንስ የአማራ ክልል መንግስት ለቅርሱ ጥገና አገልግሎት የሚውል 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዳደረገና የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ደግም 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የላሊበላ ቅርስ የተሰራበት ጥበብ ሀገር በቀል መሆኑና ይህ ጥበብም በአሁኑ ጊዜ አለመገኘቱ፣ በዓለም አቀፍ የሚገኘዉ የቴክኖሎጂ ጥበብም ይህንን ሀገር በቀል ጥበብ የማይተካዉ መሆኑ እና የገንዘብ ችግር መኖር ለችግሩ በፍጥነት መፍትሄ እንዳይሰጥ ያደረጉ ተግዳሮቶች መሆናቸዉ በመግለጫው ተመላክቷል።

ይሁን እንጂ አነዚህ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፥ የቅርሱን የዓለት ስንጥቆች ሊያያይዝ የሚችል ቴክኖሎጂ መገኘቱንና ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ለቅርሱ ጥገና የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ ከመንግስት፣ ከማህበረሰቡ እና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ ምክር ቤትም ከላሊበላ ቅርስ የሚበልጥ ስለሌለ ለቅርሱ ጥገና የሚውል ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የቅርስ ጥገና ስራዉ ከመጀመሩ በፊትም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ከሚገኙ የምህንድስ ባለሙያዎች እንዲሁም የቅርሱ ባለቤት ከሆነዉ ከዩኔስኮ ጋር ውይይት የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም ስራዉን ለማስጀመርም ዓለማቀፋዊ ጨረታ የሚወጣ በመሆኑ፥ በዚህም ምክንያት የተወሰነ መዘግየት ሊኖር እንደሚችል አቶ አክሊሉ ተናግረዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply