ለሓዮሎም ሃወልት መስሪያ የተዋጣውን ሚሊዮን ብር ማን በላው? ልጆቹ ወይስ የህወሓት አማራር?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(አሰገደ ገ/ስላሴ)

ይህን ጥያቄ ያነሳሁት ዝም ብዬ አይደለም። ለዚህ ጥያቄ ቀስቃሽ የሆነብኝ ሰሞኑን ኣንድ የሓዮሎም ልጅ ነው የተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያ ብቅ ብሎ ስመለከት የትምህርት እድል ያላገኜ፣ በኑሮ ችግር ምክንያት ሰውነቱ የከሳ ፊቱ የገረጣ ስመለከት ብዙ ጥያቄዎች ጫረብኝ።

1ኛ ይህን ልጅ ስመለከት ኣሁን በጭንቀት ያሉ የህዋሓት ኢህኣደግ መሪዎች ልጆች ግማሾቹ የትላልቅ ኩባንያ ባለቤት ሆነው፣ ግማሾቹ በአሜሪካ ስቴቶች፣ በቻይና፣ በኣውሮፓ በሌሎች የበለጸጉ ሀገራት በሀገር ሀብት በከፍተኛ ገንዘብ የተገዙ መኪና ይዘው፣ የቤት ባለቤት ሆነው በምርጥ ት/ ቤት በከፍተኛ ክፍያ ሲማሩ ስመለከት በሃገራችን ያለውን ኣድላዊ ስርኣት ይነግረኛል።

2ኛ እንደ የሓዮሎም አርአያ ልጅ ያሉ ጧሪ ኣጥተው ከ360 000 ወጣቶች በላይ ፣ ከ126 000 በላይ ኣካል ጉዳቶኞች ባሉበት ትግራይ በኣሁኑ ጊዜ ደግሞ እያሉን ያሉ ኣሁን የግፍ ኣገዛዛችንና የኣሰቃቂ ስራችን ለማስቀጠል ደቡቁን እያሉን ነው ። ግን ኣይቻልም የኢትዮጱያ ህዝብ ነቅቷልና ።በተለይ የትግራይ ህዝብ ጥቂት ተጠቃሚ ቅጥሮኞች ካልሆነ በስጠቀር ብዙሃኑ የትግራይ ህዝብ ከእንግዲ መደበቂያ ምሽግ ኣይሆንም ሊቀበላቸው ኣልቻለም በመሆኑም በጭንቀት ስላሉ ለጭንቀታቸው እና ለስጋታቸው እንደ መፍትሄ ብለው ኣዲስ ሃሳብ በመፈልሰፍ ይንቀሳቀሱበት ያሉ ረስቶዋቸውና ክድቶዋቸው የኖሩ የተሰው ታጋዮች ልጆች እነስዩም መስፍንና ስብሃት ነጋ የማያፍሩ ደመላሽ ወይ ባለኣደራ በሚል ስያሜ ኣዳራጅተው ዘበኛ ሊሆኑዋቸው የውሼት ታሪክ እየደረደሩ ቢሰብኩ ወይ በማህበር ለመደራጀት ቢሞኩሩም በጥቂት ተጠቃሚዎች ካልሆነ በስተቀር በኣብዛኞቹ ግን ተቀባይነት ኣጥተዋል ።

3ኛ እነዚህ ሰዎች የክዳት ክዳተቸው የሚያሳየን ሓዮሎም ማንገደለው የሚለው ለታሪክ ተማራማሪዎችና ጸሃፋዎች እናስቀምጠውና ሓዮሎም ከሞተ በኃላ ለሓዮሎም ሃወልቲ መስርያና ለሉጆቹ መጦሪያ ተብሎ ከሃገር መካላከያ ሰራዊት ከክልሎች ከህዝብ በቡዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተዋጥቶ ነበር ።

የተዋጣው ገንዘብ በወቅቱ ይነገር እንደነበረ መዋጮው ሳይጠቃለል ከ16 ሚሊዮን በላይ ደርሶ እንደ ነበር ኣውቃለሁ መዋጮው ከኣንድ ኣመት በላይ ቀጥሏል ። የተዋጣው ገንዘብ የበላይ ተቆጣጣሪ ስብሃት ነጋ ነበር ።

በሓዮሎም ስም የተሰራ ኣዲነብሪኢድ በኣባቱ ወጀድ የሚገኜው ኣስከሪዮኑ ካረፈበት እንዳ እየሱስ ከሚባል ቤተክርስትያን ኣጠገብ መቃብር ኣትለውም ሓወልትም ኣይባልም የድንጋይ ክምር ተቀምጦ የስራ ጥራት ስለሌለው ሁሉ ጊዜ ስለሚፈርስ በኣመት በኣመት ይጠገናል ። ለሀወልቱ የወጣ ገንዘብ ከኮንትራክተር ጸጋይ ደሞዝ የተፈጸመ ውል 1 .5 ሚሊዮን ብር ነው የሃወልቱ ዋጋ የተቀመጠ ግምትና የስራ ኣይነት በወቅቱ ከነበረ የኮንስትራክሽን እቃዎች ርካሽ ስለነበር መሃንዲሶች ቢያጠኑት ከ300 000 በላይ ብርም ኣይጨርስም ።ግን ሁሉም ነገር በስብሃት የሚጨረስ ስለነበር ምንም ለማድረግ ኣይቻልም ነበር ።

ሓወልቱ በቤቱ በቤተክርስትያን መሰራት የለበትም ቢሆን ኣዲስ ኣበባ በወረደ በመቐለ ባነሰ በሽረ እዳህላሰ ይሰራ የሚል ጥያቄ ከራሴ ጀምሬ ቡዙ ጓዶች ጥያቄ ኣንስተን ነበር በነስብሃት ነጋ ኣባይ ጸሃዬ ሌሎችም ግን ቁጣን ፈጠረ ። ሃወልቱ ከተሰራ በኃላ በሸረ ኣውራጃ ህዝብ ብሎም በትግራይ ህዝብ በተለይ በታጋዮች የሓዮሎም ሃወልቲ ለምን ተደበቀ የሚል ጥያቄ በረታ በተለይ የኣድያቦ ህዝብ ተቆጣ ። ።የሓዮሎም ሃወልት ለማዬት ከሩቅ ቦታ የመጡ ኢትዮጱያውያንም ቢሄር በማይለይ ጥያቄው ያነሱ ነበር ግን ሰሚ ጆሮ ኣልነበረም ።

ኣሁን በሽሬ ያለው በሃሓዮሎም ኣደባባይ በሚባለው ቦታ በሃገር መከላከያ ምኔስቴር ወጭና መሃንዲሶች የተሰራ ሀወልትም 1ኛ ሰራዊቱ የሓዮሎም ሃወልቲ ለምን ተደበቀ የሚል ጥያቄ ስለ ተቀጣጠለ 2ኛ በወቅቱ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስለነበረ ለወጣቱ ለመነሳሳት ታሳቢ በማድረግ ሳይወዱ በግድ የተሰራ ነው እንጅ እንደ የህወሓት መሪዎች ኣመለካከት የሓዮሎም ሀወልቲ እና ማንነት ወደ ኣደባባይ እንዲወጣ ኣይፈልጉም ነበር ።

ለዚሁ ለመረጋገጥ ኣንድ ነገር የህወሓት ሓዮም ማንነት እንዳይ ታወቅ የሚፈልግ መሆኑ የተጋለጡበት ለማስረጃነት ያህል ባለፉት ኣመታት ኣንድ ሰሎሞን ገብረኣረጋዊ የሚባል ጸሓፊ ስለሓዮሎምና የኣባቱ የኣያቱ ቀደምት ኣያቱ ኢትዮጱያዊ ወገንተኝነት በጥልቀትና በስፋት የሚተነትን መጽሃፍ በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈ ዳግመ ኣሉላ የሚል ፣በኣማርኛ ቋንቋ የተጻፈ የሓዮሎም ገድል የሚሉ ሁለት መጻሀፍት ጽፎ ለማስመረቅ ለቡዙ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ እና ካድሬዎች የመንግስት ባለስልጣናት ህዝብ በመቐለ ሚላኖ ሆቴል በኣዲስ ኣበባ ኣክሱም ሆቴል ጠርቶዋቸው ኣንድም ባለስልጣን ኣልተገኜም ሌላ ቀርቶ የሓዮሎም እህት የኢህኣደግ የፓርላማ ተቀማጭ የሆነች ወይዘሮ ኣልማዝ ኣርኣያ ለሌላ ስራዋ መቐለ መጥታ እያለች በመጽሃፍ ምርቃኑ ከኣባይ ወልዱ ጋር ሆና ሪባኑ ልትከፍት ተጠርታ ለሆዳ ስትል ፈርታ ኣልመጣችም ምን ታድርግ የህወሓት መሪዎች ለብዙ ሰው በሆዱ ይዘውታልና ። በኣዲስ ኣበባም እዛው እያለች ኣልመጣችም ሌሎችም ኣልመጡም ። መጽሃፎቹ እንዳይሸጡም ቡዙ ተጽእኖ ኣድርገዋል ። ይህ እዬሆነው ያለው በህወሓት መሪዎችና በሓዮሎም ኣርኣያ የነበረ ግንኝነት ምን እንደነበር ያጠራጥራል ።ሃዮሎም ማን ገደለው የሚልም ጥያቄ ይጭራል ።

የተከበራቹ ኣንባብያ የህወሓት ኢህኣደግ መሪዎች በተለይ ስብሃት ነጋ ኣባይ ጸሃዬ ፣ስዩም መስፍን ፣ጸጋይ በርኸ ፣ኣባይ ወልዱ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ኣዲሱ ለገሰ፣ መለስ ዜናዊ ሌሎችም እጅግ ቡዙ ዘርን የሚቀሰቅሱ ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩ ቁሻሻ መጻህፍት በሸራቶን ፣በሂልተን ፣በኣክሱም ሆቴሎች ኣዲስ ኣበባ በመቐለ በሃወልት ሰመኣታት ፣ በኣክሱም በፕላኔት ሆቴሎች ወ ዘ ተ ኣዳራሽ መርቀዋል ።መቸ መመረቅ ብቻ እነሱ የመረቁት ያጻፉት መጻህፍት ሲሸጡም በሁሉም የኢትዮጱያ ቢሮወች የመንግስት ሰራተኞች ትምህርት ቤቶች ፣በሃገር መከላከያ ሰራዊት በግድ በብድር ከደሞዛቸው የሚቆረጥ መቁረጥ ፣ለጻፊዎች መሸለም የትምህርት ስኮላር መስጠት ድረስ ሄደዋል ።ሃቀኛ መጻህፍት ግን በሙሉ ለህወሓት መሪዎች ጠላቶች ናቸው ።

ኣሁን የሓዮሎም ልጆች የት ኣሉ ? በኣባታቸው ስም ለሃወልቲ መስሪያ ለልጆቹ ማሳደግያ ተብሎ የተሰበሰበ በኣስር ሚሊዮን የሚቆጠር ብር በህዝብና በታጋይ ገቢ የሆነ ገንዘብ የት ገባ ? ከታጋያዋ የተወለዱ ሁለቱ እናታቸው ወደ መሪካ ኢባሲ በመመደባ ኣመሪካ ከእናታቸው ጋር ሄደው ምንደረጃ እዳሉ ኣላውቅም ምናልባት ኣንዱ የጀነራል ጻድቃል ልጅ ተድሮ እዳለ ይነገራል ኣንዱ በኣመሪካ እንደ ሃገሩ ሸቅሎ እንደሚኖር እሰማለሁ ትምህርትም እንዳልጨረሰ እሰማለሁ ።

ሰወስተኛው ከኣፋር የተወለደው በትምህርትም ቡዙ እንዳልተራመደ በንሮም እናቱም ሞታ በፊቱ የሚታይ ሆኖ የሌሎቹ የተሰው ታጋይ እጣ ፋንታ ደርሶታል ። የኣባታቸው ገንዘብ የትገባ መልሲ የምትፈልጉ ለስብሃት ነጋና ለሌሎች የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጠይቁ ። በመጨረሻ ግን ለሓዮሎም ልጅና ለሌሎች የተሰው ታጋይ ልጆች የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋ ።

Share.

About Author

Leave A Reply