ለመሆኑ ታምራት ደስታ ማን ነው?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከጥቁር ውሃ እስከ ሚኒልክ ሆስፒታል

ድምጻዊ ታምራት ደስታ ከሐዋሳ አጠገብ በምትገኘው ጥቁር ውሃ በምትባል ትንሽዬ መንደር ተወለደ። ታምራት ሁለት ወንድሞች ያሉት ሲሆን የቤተሰቦቹ ሁለተኛ ልጅ ነው።

ታምራት የሃይስኩል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ቤተሰቦቹ መኖሪያቸውን ወደ ሻሸመኔ ከዛም ወደ ሐዋሳ አደረጉ።

በ1990 ዓ.ም ታምራት ከአሳዳጊዎቹ ጋር ለመኖር ወደ ድሬደዋ በማቅናት ጨርቃጨርቅ የኪነት ቡድንን ተቀላቅሏል። ጨርቃጨርቅ የኪነት ቡድን በነበረው ቆይታ አንድ ድምፃዊ ከባንድ ጋር ሆኖ እንዴት ሙዚቃ መጫዎት እንዳለበት የሚረዳውን ስልጠና ተከታትሏል።

ታምራት በጀመረው የሙዚቃ ስራ ለመቀጠል በ1991ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጣ። ከዛም “ከሀኪሜ ነሽ” ነጠላ ዘፈን በማስከተል በ1996 ዓ.ም “አንለያይም” የተሰኘ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን ለህትመት አበቃ።

አንለያይም አልበም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን የዚህ አልበም በርካታ ግጥሞች በጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለ የተፃፉ ሲሆን የስድስት ዘፈኖች የዜማ ደራሲ ራሱ ታምራት ደስታ ነው።

ታምራት ከበርካታ ነጠላ ዘፈኖች በተጨማሪ “ከአንቺ አይበልጥም” እና “ከዛሠፈር” የተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን አድርሷል። አዲስ አልበሙን ለማውጣትም በዝግጅት የነበረ ሲሆን በ39 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ድምፃዊ ታምራት ደስታ ዛሬ ማለዳ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ወደህክምና ተቋም ቢያመራም ህይዎቱ ግን ሊተርፍ አልቻለም።

የህልፈቱ ምክንያት ምንእንደሆነ ያልታወቀ ሲሆን በሚኒልክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ በመደረግ ላይ ነው። የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

ታምራት ደስታ ባለትዳር እና የ6ልጆች አባት ነበር።

ለቤተሰቦቹ፣ ለስራ ባደረባዎቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅፅናናትን እንመኛለን።

 

Share.

About Author

Leave A Reply