ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚጫወተው ፋሲል ከነማ የታንዛንያ አቻውን አዛም ክለብን አሸነፈ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተጫወተ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ከታንዛንያው አዛም የእግር ኳስ ቡድን ጋር ተጫውቶ በመጀመሪያው 45 የማጠናቀቂያ ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፏል፡፡

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የተጫወተው ፋሲል ከነማ በ2ኛው አጋማሽ ጫና ሳይፈጥር በዛብህ መለዮ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፏል፡፡ የመልስ ጨዋታውን ወደ ታንዛንያ ዳሬሰላም ተጉዞ ከ15 ቀናት በኋላ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ጨዋታውን ሱዳናዊ ዳኛ መርተውታል፡፡ በጨዋታው አዛሞች አምስት የማዕዘን ምቶችን ሲያገኙ በአንጻሩ ፋሲል ከነማ አንድ የማዕዘን ምት ብቻ ነው ያገኘው፡፡
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ፋሲል ከነማ በረኛውን በጉዳት አጥቷል፤ በምትኩም ተቀያሪ በረኛ ጀማል ጣሰውን ተጠቅሟል፡፡ የፋሲል ድል ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያው ድል ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply