ለማና አብይ እራሳቸው [የለማንና አብይን] አብዮት ወደ ዘረኛነት] እየቀለበሱት ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“…..ነገሩ በንግግር ደረጃ መገርሳንም ስሰማ (በተለይ ለማ መገርሳ!) በዘር ፖለቲካ ላይ በጣም ጫን ብሎ ተቃውሞ ድምፅ ያሰማ ይመስለኛል እኔ እንደሰማሁት። አብይ እንደሱ [እንደ ለማ] ያህል ባይሰማኝም እሱም አንድ ላይ ናቸው ያሉት።

ነገር ግን ይህ ዲስኩር ነው። ስኩር ደረጃ ግሩም ናቸው:: በተግባር ደረጃ ግን የሚሰራው የምናየው ሹመቱንም ምኑንም ስንመለከት የምንገንዘበው እልተለውጥንም:: ያው ነው:: መንግዳችን ያው ነው:: የዘር መንገድ ነው የያዝነው:: ላለፉት 40 ዓመት ከሄድንባቸው ጉዞ እንዲያው መንጥቆ የሚያወጣን ደረጃ ላይ ደርስን ስንል ቀስ ቀስ እያለ እንደገና የሚደፍቀን ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው:: እናም አሳዛኝ ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ ይመስለኛል።

የእነ ለማና አብይ አብዮት እተቀለበሰ ነው ለማለት ይቻላል [ይመስለኛል]። ደግሞ ሌላ ስው ቀልብሶባችው አይደለም። እራሳቸው [ለማና አብይ] እየቀለብሱት ነው።

(ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

Share.

About Author

Leave A Reply