ለምን ታከለ ኡማ መነሳት እንዳለበት ግርማ ካሳ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ልጆች እንጂነር ታከለ ኡማ ከሃላፊነቱ እንዲነሳ ጠይቀዋል። እኔም ይሄንን ጥሪ አስተጋባለሁ። በሶስት ምክንያቶች ፡

አንደኛ – ኢንጂነር ታከለ ወደ ሃላፊነት የመጣው ፣ እርሱን ለማስመረጥ አሻጥር ተሰርቶ ነው። የከተማ ከንቲባ የሚመረጠው ከከተማዋ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ነበር። ሆኖም ኢንጂነር ታከለን ለማስመረጥ ፓርላማው የአዲስ አበባን ምክር ቤት ሕግ እንዲቀየር ተደረጎ ነው የተሾመው። ሕገ ወጥ በሆነ አሰራ። ልክ በመቀሌ ዶር ደብረጽዮን እንደተመረጠው።

ሁለተኛ ኢንጂነር ታከለ ከንቲባ ከመሆኑ በፊት በአዲስ አበባ ላይ ጽንፈኛ አመለካከት ነበረው። ፊንፊኔ የሚላት አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ብሎ ነበር የሚያምነው። በቅርቡ ከንቲባ ከሆነ በኋላ አዲስ አበባ የሁሉም ናት አለ። ግን ለማስመሰል ያለው እንጂ የአመለካከት ለውጥ አድርጎ አይደለም።

ኦነግን ለመቀበል በተደረገው ዝግጅት በኦሮምኛ የተናገረው ተተርጉሞ አነበብኩ። እንደሚታወቀው አንዳንድ የኦሮሞ ቄሮዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ነቅለው በጀብደኝነት የኦነግን ለመተካት ሲሞክሩ ግጭቶች ተፈጥረው ነበር። ግጭቶችን ለማረጋጋት ፖሊስ ለተወሰነ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገቡ ወገኖች እንዲቆዩ በማድረግ ግጭቶች እንዳይባባሱ ለማድረግ ሞክሯል።፡በኋላም ሁሉም ገብተው በሸገር ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ሆኖም ኢንጂነር ታከለ ግጭቶች እስኪረጋጉ ለሰላም ሲባል የተወሰደውን ጊዚያዊ የመንገድ መዝጋት እርምጃ፣ በኦሮሞ ላይ በደል እንደተፈጸመ አድርጎ ነበር ያቀረበው። በዚያ የነበረው ኦሮሞ በደል ደረሰብኝ ብሎ እንዲሰማው ነው ያደረገው። ከማረጋጋት፣ ከማሰባሰብ፣ አንድ ከማድረግ ይልቅ የአዲስ አበባን ህዝብ ነው በኦሮምኛ የከሰሰው።

” ከዋዜማ ጀምራችሁ የዉሃ ጥማት ሳይበግራችሁ ርሃብ ሳያስቸግራችሁ፣ ብርዱ ስይበግራችሁ ስድብ ሳያስቸግራችሁ፣ አትገቡም ብትባሉ እንኳን ሳትበገሩ ..እንኳ ንወደ ግዛታችን ወደ አባቶቻችን እምብርት ሃገር በሰላም መጣችሁ” ሲል ነው ኢንጂነር ታከለ ተበዳይ፣ ጻድቅ ቄሮ፣ በዳይ፣ ተሳዳቢ የአዲስ አበባ ወጣቶች አድርጎ የሳለው።

አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ናት ሲል የነበረው ኢንጂነር ታከለ፣ በኦሮምኛ በሃሺሽ የሰከረ ይመስል፣ በስሜት “እንኳን በፊንፊኔ ዛሬ ተገናኘን። ለፊንፊኔ ተብሎ ብዙ ሰው ታስሯል። ተሰቃይቷል።ከሃገር ተሰዷል። በአባቶቻችን ሃገር ቀና ብለን መሄድ እየቻልን እየፈለግን ከዩኒቨርሲቲ ተባረናል። ዋጋ ለፊንፊኔ ከፍለናል” ሲል ፊንፊኔን የኦሮሞ መሬት እንደነበረች፣ ተነጥቀው እንደነበረና አሁን ግን በእጃቸው እንደወደቀች አይነት የ”ድል” ንግግር ነበር ያደረገው።

ሶስተኛ – ኢንጂነር ታከለ የ እቴጌ ጣይቱ ሃዉልት እንዲሰራ ከተወሰነ በኋላ ፣ እነ ጃዋርና እነ ጸጋዪ አራርሳ ያሉ የጥፋት ዘረኛ ሃይሎችን የጓሮ መመሪያ ተቀበሎ ፣ የአዲስ አበባ እናት የሆንችዋን የ እቴጌን ሃዉልት እንዳይሰራ አግዷል።

በአጠቃላይ ኢንጂነር ታከለ ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ የመሆን መብት አለው። ምርጫ ሲደረግ እትወዳድሮ መሆን ይችላል። ሆኖም ግን አሁን በሹመት የአዲስ አበባን ህዝብ ፍላጎት ያስጠብቃል ብዬ አላምንም። የአዲስ አበባን ህዝብ ይመጥናል ብዬ አላምንም። አዲስ አበባ መተዳደር ያለባት በአዲስ አበቢዎች እንጂ በኦህዴድ ሹመኞች ነው ብዬ አላምንም። አዲስ አበባ ራሷን በራሷ ማስተዳደር፣ የራሷን እድል በራሷ የመወሰን መብቷ ተጠብቆላት፣ ከኦህዴድ ሞግዚትነት መውጣት አለበት የሚል ጠንካራ አቋም አለኝ። በመሆኑም በአዲስ አበባ ድምጻቸው ያሰሙ ወገኖች ጥያቄ የኔም ጥያቄ ነው። ኢንጂነር ታከለ ኡና በአስቸኳይ መነሳት አለበት።

አንዳንድ ዘረኞች ታከለ ኦሮሞ ስለሆነ ነው ይላሉ። ጎበዝ እኛ ኦሮሞውን ዶ/ር አብይ፣ ኦሮሞዉን አቶ ለማ የደገፍን ነን።

Share.

About Author

Leave A Reply