ለአርቲስ ፈቃዱ ተክለማርያም በጎ-ፈንድ ሚ የተሰበሰበ 76 ሺህ ዶላር የት እንደደረሰ አልታወቀም።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በታዋቂው አርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያም ስም የተሠበሠበው ገንዘብ በተመለከተ የፊታችን አርብ ጥቅምት 23 መግለጫ ሊሠጥ ነው። ከገንዘብ አሠባሳቢ ኮሚቴው አባላት አንዱ ለዘሀበሻ እንደተናገሩት በጎፈንድ ሚ ለአርቲስቱ ህክምና ከ76 ሺ ዶላር በላይ ቢሠበሰብም እስካሁን ለማንም አልተሠጠም።
ለአርቲስቱ ሕክምና ተብሎ ገንዘቡ ከተሠበሠበ በኀላ በገንዘቡ ህክምና ሳያደርግበት ፀበል እያለ ለህልፈት መዳረጉ ይታወሳል። ከጅምሩ በጎፈንድ ሚ ገንዘብ የማሠባሠቢያ አካውንት የተከፈተው ከኮሚቴው እውቅና ውጭ ነበር ያሉት እኚሁ ሰው የፊታችን አርብ ለጋዜጠኞች ለማብራራት እንዳሠቡ አስረድተዋል ።
አርብ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ጋዜጠኞች በአፍሮዳይት ሆቴል ተገኝተው እንዲከታተሉም በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

Share.

About Author

Leave A Reply