ለአዲስ አመት የተጀመረውን የአዲስ ተስፋ ቀመር የስጦታ ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ለ600 ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተነገረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለአዲስ አመት የተጀመረውን የአዲስ ተስፋ ቀመር የስጦታ ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ለ600 ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተነገረ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆየውን ይህንኑ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልን ጨምሮ ሁሉም የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማት እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡የኩላሊት እጥበት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ እንደነገሩን አገልግሎቱ የሚሰጠው ድርጅታቸው ከሆስፒታሎቹ ጋር በፈፀመው የወጪ መጋራት አሰራር አማካይነት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ድርጅታችን ስድስት መቶ ሺህ ብር ወጪ ያደረገ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በሆስፒታሎቹ የተሸፈነ ነው ተብሏል፡፡በተለያዩ ሆስፒታሎች በሳምንት እስከ ሁለት ሺህ ብር ድረስ ይከፍሉ የነበሩ ህሙማን በጊዜው ገንዘቡን ለበዓል እንዲጠቀሙበት በማሰብ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ የበጎ አድራጎት ስጦታ ፕሮግራም ላይ ህሙማኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጎብኝተው ያበረታቷቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም አንድም ባለስልጣን ባለመገኘቱ ህሙማን ቅሬታ እንደተሰማቸው ነግረውናል፡፡
(ሸገር)

Share.

About Author

Leave A Reply