ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የውሃ አገልግሎት ክፍያ በባንክ በኩል ሊደረግ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ አገልግሎት ክፍያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ለማደረግ የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ. ም ተፈራረሙ። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ባጫ ጊና እና በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በኩል ደግሞ ዋና ስራስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ስምምነቱን አድርገዋል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባጫ ጊና እንደገለጹት ዛሬ ላይ የባንኩ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኝት የሚችሉበትን ሁኔታ መመቻቸቱን ጠቅሰው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ ለመሰብሰብ መወሰኑ አገልግሎቱን ቀልጣፋ ያደርግለታል ብለዋል።

አቶ ቶባጫ አያይዘውም የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞችም የአገልግሎት ክፍያቸውን በሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ በሌሎች ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሁሉ ክፍያቸውን በቀላሉ መፈጸም ይቻላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን በበኩላቸው በአዲስ አበባ ውስጥ ከ560 ሺህ በላይ የውሃ አገልግሎት ደንበኞች እንዳሉ ጠቅሰው ይህ ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት የሚያድግ በመሆኑ ከባንኩ ጋር ያደረግነው ስምምነት ለአገልግሎት አሰጣጥ መቀላጠፍ ያግዛል፤ ደንበኞችም ሳይጉላሉ የአገልግሎት ክፍያቸውን በቀላሉ መፈጸም ያስችላቸዋል ብለዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply