ለአዲስ አበባ አዲስ ከንቲባ ተሾመ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ
ዶክተር አምባቸው መኮንን አዲሱ የከተማችን ከንቲባ ሆነዋል። ዶክተር አምባቸው በብአዴን ለውጥ ውስጥ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ትልቅ ሚና የነበራቸው እና የኮንስትራክሽን ሚኒስትር የነበሩ ናቸው።
የትምህርት ዝግጅት
– የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
– ሁለተኛ ዲግሪ (MA) በፐብሊክ ፖሊሲና ኢኮኖሚክስ ከደቡብ ኮሪያ KDI School of Public Policy and Management
– ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በዓለም አቀፍ ፋይናንስና ኢኮኖሚ
ልማት እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣
– ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በኢኮኖሚክስእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
– ከ1983-1987 ዓ.ም ድረስ የወረዳ አመራር፣
– ከ1990-1993 ዓ.ም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ኃላፊ፣
– ከ1994-1997 ዓ.ም የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ፣
– ከ1998-1999 ዓ.ም የአማራ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣
– ከ2004-2005 ዓ.ም የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር፣
– ከ2006-2007 ዓ.ም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
– ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት በድርጅትና በመንግስት እንዲሁም ክልሉን መልሶ በማደራጀት ተቋማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች እንዲተገበሩ በመምራትና በማስተባበር ስኬታማ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ የከተማ ልማት ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ስራዎች በክልል ላስገኙት ውጤቶች አስተዋፅኦቸው ነበረበት፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply