ለዶክተር አብይ አህመድ ፋታ መስጠት የሚያስፈልገው ለእርሳቸው ስልጣን ማራዘሚያ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ተብሎ ነው (ዶክተር ዘላለም እሸቴ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“ሙያ በልብ ነው” የሚለውን መርህ ያነገቡ የሚመስሉትን እኚህን የኢትዮጵያ ልጅ፣ ማስተዋልን በተፋታ መልኩ ጥላሸት እየቀቡ መሞገት አሁን ጊዜው ነውን? ሲሉም ዶክተር ዘላለም ይጠይቃሉ።

ከፊሉ ኢትዮጵያዊ ለዶክተር አብይ ጊዜ ልንሰጣቸው ይገባል ሲል ጥቂት የማይባሉ ወገኖች ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብን ተቃውሞ በማዳፈን የአገዛዙን እድሜ ከማስቀጠል ውጭ የሚያመጡት ለውጥ ስለማይኖር ምንም ፋታ መስጠት አያስፈልግም ይላሉ።

ዶክተር ዘላለም ግን “ እነዚህ ትዕግስት የጎደላቸው ወገኖቻችን፣ የትግላቸው ስልት ጊዜውን እንዲመጥን በማደስና ከሕዝብ የልብ ትርታ ጋር በማጣጣም፣ለኢትዮጵያ ፋታ ቢሰጡ ይበጃቸዋል”በማለት ይሟገታሉ።

-ኢትዮጵያዊው አትሌት አበረታች ዕጽ መጠቀሙ በመረጋገጡ ለ4 ዓመታት ከውድድር ታገደ።

 

ከፍተኛ ሙስና የተንሰራፋበት የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ጉዳይ በሲኖዶስ ጉባኤ እንዳይታይ ፓትርያር አቡነ ማትያስ ማገዳቸው በሌሎች ጳጳሳት ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል።

በሀገረ ስብከቱየተንሰራፋው ሙስና እና ዝርፊያ ጉዳይ በአጀንዳነት እንዲካተት ከፍተኛ ክርክርና ሙግት ቢደረግም ፓትርያርኩ፣ “በሀገረ ስብከቴ አትግቡብኝ፤ ችግር የለም፤ እንዲያውም ከመቼውም ጊዜ በላይ በሰላምና በዕድገት ላይ ነው፤ ችግር ካለም እኔ ራሴው እፈታለሁ፤ ስለዚህ ጉዳዩ አይታይም፤”የሚል ግትር ውሳኔ አሳልፈዋል። በሁኔታው ከተበሳጩት አባቶች መካከል የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን ሀገረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል፦”ብጹዕነትዎ፣ሥራ አስኪያጅዎ ሌባ እና በሥርቆት የተጨማለቀ ነው። እኔ የሲኖዶስ አባል የሆንኩት እውነቱን ለመመስከር ነው።ይሔ ሲኖዶስ የሚሰበሰበውኮ ለይስሙላ አይደለም!” በማለት በቁጣ ፓትርያርኩን ፊት ለፊት ተቃውመዋቸዋል።

የቀድሞው የመንግስት ቃል አቀባይና ከቀናት በፊት የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ከሻኪሶ ወርቅ ማምረቻ ጋር በተያያዘ ዳግም የተቀሰቀሰው ሕዝብ ተቃውሞ ትክክል እንደሆነ ጠቁመዋል።

“በቦታው የሚካሄዱ ማናቸውም ኢንቨስትመንቶች ሕዝቡን የሚጠቅሙ እንጂ የሚጎዱ መሆን የለባቸውም” ያሉት የቀድሞው ዶክተር ነገሪ፣ሚድሮክ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለወሊድ ችግር መጋለጥን ጨምሮ ለሌሎች አደገኛ ህመሞች እየተጋለጡ እንደሆነ ያብራራሉ።

እነዚህንና ሌሎችን ዜናዎች እና ለእናንተው ይሆናሉ ያልናቸውን ወቅታዊ ዝግጅቶች አሰናድተን በሰዓቱ ወደ እናንተ መጥተናል።

ትንሳዔ-የእርስዎ ራዲዮ!

Share.

About Author

Leave A Reply