ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዟቸው ተገታ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ለ2018ቱ የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ የመጨረሻውን የመልስ ጨዋታ ዛሬ ከአልጄሪያ አቻውን አዲስ አበባ ላይ አድርገው 3–2 ተሸነፉ::

አልጄሪያ ላይ 3ለ1 ተሸንፈው የነበሩት ሉሲዎቹ በአጠቃላይ ውጤት 6 ለ 3 ተሸንፈው የአፍሪካ ዋንጫ ሕልማቸው ሳይሳ ቀርቷል::

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሉሲዎቹ አልጄሪያ ላይ 3ለ1 ተሸንፈው ቢመለሱም በዛሬው ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገብቶ እንዲያበረታታቸውና ውጤቱን እንዲቀይሩ የስታዲየም መግቢያውን በነጻ አድርጎት ነበር::

ሉሲዎቹ ዛሬ አልጄሪያ ላይ በ65ኛው እና 73ኛው ደቂቃዎች ያገቡትን ጎል ያስቆጠረችው ሎዛ አበራ ነበረች::: አልጄሪያዎች ቀድመው ሶስት ጎሎችን አስቆጥረው የነበረ ቢሆም ሉሲዎቹ ጨዋታቸውን ቀይረው የጎል ልዩነቱን አጥብበውታል::

Share.

About Author

Leave A Reply