ሌላኛው ታከለ ኡማ በንግድ ባንክ (ነገሰ ተፋረደኝ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠ/ሚ ዐቢይ በቃሉ የተባለን ሰው አንስቶ የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ምክትል ፕሬዝደንት የነበረውን አቶ ባጫ ጊኒን የንግድ ባንክ ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ይህ ሰው እንደተሾመ ያደረገው የኦሮሞ ባለሀብቶች ሌላ ባንክ ላይ የተበደሩትን ብድር መግዛት ነው። የሌሎች ባንኮች የብድር ወለድ ጣሪያ እስከ 18 በመቶ ይደርሳል። የንግድ ባንክ ደግሞ 11 ነጥብ 5 ነው። 18 % የብድር እርከን ካለው ባንክ ለንግድ ባንክ ብድር የተገዛለት ባለሀብት ከ7% በላይ ብድር ቀነሰለት ማለት ነው። ይህ አንዱ ማሳያ ነው።

ንግድ ባንክ ላይ በሁለት ሶስት ወራት እየተሰራ ያለውን ነገር የሚገልፀው አፓርታይድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊባል አይችልም። ጠ/ሚ ዐቢይ ባጫን ከሾመ በኋላ ንግድ ባንክ ላይ እየተሰራ ያለው ጉዳይ ቢጣራ ሕወሓት ሲሰራው ከኖረው ቢብስ እንጅ የሚያንስ አይደለም።

ታከለ ኡማ መታወቂያ ሲያድል፣ የከተማዋን የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር ቀና ደፋ ሲል ሌላኛው ታከለ ደግሞ የባንክ ስርዓቱ ለመቀየር እየሰራ ነው። ዛሬ 7 ምክትል ፕሬዝደንቶች በባጫ ምክንያት መልቀቃቸው ታውቋል።

Share.

About Author

Leave A Reply