ልዕልት ሳራ ግዛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ልዕልት ሳራ ግዛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ልዕልት ሳራ የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ልጅ የልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ ባለቤት፣ የንጉሡን አመራር የሚቃወሙ የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎች ንቅናቄ አመራር ከነበሩት አንዱ የነበረውና አፍንጮ በር አካባቢ የተገደለው የጥላሁን ግዛው ታላቅ እህት ነበሩ።

በ1920 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት ይህቺ ውብ ልዕልት እቴጌ መነን ካለፉ በኋላ በእሳቸው ምትክ የንጉሱ ልዩ አጃቢ በመሆን ወደ ተለያዩ ግዛቶች በመጓዝ አገልግለዋል። እንዲሁም በእንግሊዝ አገር በነርስነት ሙያ ተመርቀው እንደ ልዕልት ፀሐይ በኢትዮጵያ ውስጥ በግዜው በነበሩት በተለያዩ ሐኪም ቤቶች በመዘዋወር ያለምንም ክፍያ በራሳቸው ፍቃድ የበጎ አድርጎት አግልግሎት ለህብረተሰቡ ያበረከተቱና የተለያዩ የውጭ ሃገራት ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ስለነበራቸው የቤት መንግስት አስተርጓሜ ሆነውም ያገለገሉ ታላቅ ሴት ነበሩ።

በደርግ ለአስራ አምስት አመታት በእስራት ያሳለፉት ልዕልት የኖሩበትን ፊውዳል ስርዓት የማይወክሉ ይህቺ ውብ ልዕልት በዘመናቸው ያደረጓቸው ከዋጋ በላይ የሆነ ልባዊ አስተዋጾ ለአሁን ትውልድ ሴቶች አርአያ ይሆናል።

(ጴጥⶂስ አሸናፊ)

Share.

About Author

Leave A Reply