ሕወሓት ምነው ወደላይ ሸናች?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከመኳንንት ታዬ
ሃገር መሰርት ያደረገችው ማገርም ቋሚዋም ትውልድ ነው ።ትውልድ ደግሞ በየዘመናቱ ይመጣል እና ይሄዳል።በዚህም ምክንያት ዘመናት መቀየር ህይወት ውጣ ውረድ በሰው ልጆች እና ለሰው ልጆች በሚሆን እጣ ፋንታ ሁሉ ሊሆን ግድ በሚለው ፍሰት ውስጥ ሁሉም ያሰልፋል ።ጥሩ ታሪክ ያልፋል ።መጥፎ ታሪክ ያልፋል።በዚህ ውስት የዘመኑ ዘዋሪ እና ተተኪ ጥሩ የሚባሉ ትውልዶች የሃገር ግንባታ በፍጹም መልካምነት ነገ ለሚነሳ እና ለሚተካ ትውልድ ቄዬ መስርቶ ሃገር ሰርቶ እንካችሁ ማለት የኗሪው ትውልድ እዳ ብቻ እንዳይሆን ተፈጥሮ ያስገድዳል።በዚህ ምክንያት ትላንት አለ።በዚህ ምክንያት ነገ አለ። ባዚህ ምክንያት ዘመናት አመታት ወራት እያለ ሁሉም አሉ።ይህ ነው የትውልድ ፍሰት በዘመን እስራት በሃገር ባለቤትነት በዜግነት ክብር ተጎናጽፎ ግዜን እየቀዘፈ ሁሉም ቦታ ቦታውን ይይዛል ።ያለፈው ዘመን የቀደሙት አባቶቻችን የስራ ውጤት ነበር።የዛሬው ትውልድ የሚመሩት አንጋፋዎቹ አድሉን ሊወስኑለት እጣ ፋንታውን ሊያካፍሉት የዘመኑ ታላቅ መባል ፍላጎታቸው መሆኑን ሊያበስሩት ሁሉም አንደ ትላንትን ሁሉ ዛሬ ይኸው አሉ።ግን ብርሃን አለ ማለት ብቻ ሳይሆን ባስተውሎት የተቓጠለ ሻመ፣አ ሆኖ ማብራት የፊት ለፊት ሰዎች ተቀዳሚ አሳቤ ነው።

አዎ ይህን ለመንደርደሪያ ያነሳሁት ዘመን በእኛ ሃገር ቀናትን ተክቶ ወራትን አምጥቶ፤አማታትን አሙልቶ፤ከመሃል ቢይዙት ከዳር ሳይጨማደድ፤ከዳር ቢያንጠለጥሉት ከመሃል ሳይቀደድ እግዚያብሔር ሁሉን እንዳደለ ፤ሌላው አለም እንደሚኖር እኛም እየኖርን ትላንትን ተሻግረን ዛሬን ደረስን ።ዛሬ ምንዛሬው ብዙ ነው ።በዚህ አቁማዳ ውስጥ ብዙ ብስል ከጥሬ አለ።የመጣንበት መንገድ ቅርቡም ይሁን እሩቁ ብዙ ጋሬጣዎች በዘመኑ የትውልድን እድገት በመንገድ ላይ ቆሞ ዘመናችንን እየሰየፈ የፊታቸውን ሳያዩ ሁሉ እንደነበሩ አከተሙ።አዎ በኃይለስላሴ አስተዳደር የተበሳጨው ደርግ መጣ ።መጣ እና መጣብን ያሉ የትላንት መጪዎች የዛሬ መጣብን ባዮች ተፈጠሩ።ጥያቄው ለምን መጡ አልነበረም ።በመምጣታቸው እንማን ተጠቀሙ ነው ጥያቁው ።አዎ መልሱ ዝርዝር የለውም ።መለሱን ለማግኘት ያሳለፍነውን ሃያ ሰባት አመት መለካት ከበቂ በላይ ነው ።አነባን።ተሸማቀቅን ።ትውልድ ከሰመ።ላማያውቀው በማያውቀው ሱስ እና የግብረሰዶም አባል ሆነ።ወላጆች ቅን አሳቢ ልጆቻቸውን በሱስ ተቀሙ።አዛውንቶች አንቱ እንቱ እንዳይባሉ ታሪክ ያቃሉ ትውልድ ያስተምራሉ እየተባሉ በ አባሳ ተጠቀሙ፤በቁማቸው ተመተሩ።ሃገር የኑሮ ጓያ ሰበረው እና የሃብት ብዛት ያጎበጠው ብቻ እንዲኖርባት ተደርጎ ፤ባህሉን ማክበር ፤አሴቶቹን መንከባከብ እንዳይችል ሆኖ አብሮነቱ ፤እቁቡ፤ እድሩ ፤ማህበሩ ብቻ ሁሉም በጥፍነጋ ጉራጅ ፖለቲካ እና በብተና ምስቅልቅሉ እንዲወጣ ሆኖ ማንም ማንንም ዞር ብሎ እንዳያይ ተማምሎ አብዛኛው በቁሙ አሽለበ።

ድህነት፤ ርሃብ፤ አድርባይነት ብሎም ክህደት እንደመርዝ ሁሉን ያቅበዘብዘው ጀመር ።ከቤተክህነት አስከ-ቤተመንግስት ሌብነት፤ዘረኝነት እና ጎጠኝነት እንደ አንገት ሃብል የሚያጠልቁት ወድ ሃብት ሆነ።ምኩስና ይሄን አለም ክጃለው ቢሚሉት ሳይቀር የመንገዱ ባለቤቶች የችግሩ ባለቤቶች ሆነው ፤ህይወት የሚሉትን ሰማያዊ መንግስት የሞኞች እና የጅሎች መሰባሰቢያ ሃገር አስመሰሉት ።አዎ ትላንት በጣም ብዙውን አሳት ተረግጣናል ።ዛሬም አልጠፋ ብሎን ተቸግረናል።ማን እውነት አንደተዛለ ጠፍቶን ትላንት የመንደር ፖለቲከኞች የፈበሩኩአቸው በሞታቸው እየተመነዙሩ የፈጣሪዎቻቸውን ኪስ መሙያዎች የሆኑ ትውልዶች መንገዱን እንዳሸን ሞልተውት ሁሉም እየተደናቀፈ መውድቅ የእለት የኑሮ ባህሪ ሆነ። አዎ ሃገር እንዳትፈርስ የሚታገል ትውልድ፤ሃገርን ለማፍረስ የሚታገል ትውልድ፤ሃገር ስትፈርስ አሱ እንደሚጠቀም አምኖ የተቀመጠ ትውልድ ተፈጠረ።ይሁ ሁሉ የሃያሰባት አመት በረከታችን ነው ።አንጅማ ያለመንግስት የሚተዳደር ህዝብ ተረክቦ መንግስት ሊያስተዳደርው አስከሚያቅተው ድረስ ችግር የሆነ ህዝብ እንዴት ተፈጠረ?አዎ ይህ ሁሉ የዜሮ ድምር ፖለቲካው ጭፍን የሆ ጥላጫ የፈጠረው ፤ወደር የማይገኝለት የበታችነትስሜት ያመጣው ውጤት ነው።

ይህ ሁሉ ሆነ።ትላንትም ዛሬም ተነባብረው ያለውን አቆይተው ይኸው ዋጋ እየከፈልን ባለንበት ሰአት ህልሙን ሳይከወንለት ኢትዮጲያን ከትከሻዋ ላይ የወረደው ህወሃት ዛሬ ደግሞ ስለምን በአዲስ መፈክር ተቀላቀለን።ስለምን የጦርነት ድቤ እየመታ ተቸገርን?።በውኑ ውድቀት ልኩ ስንት ነው ?።ከትላንት ለመማር ነገ መቼ ነው ?ሃገርን ሰፍሮ ሸጦ ኪስን ከሞሉ በኋላ አኔ ከሞትክ ሰርዶ አይብቀል ብሎ ወደላይ መሽናትን ምን አመጣው?።

በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በኪሳችሁ አስቀምጣችሁ ስታበቁ ለእናንተ ነገ ዛሬ ላይ የበቀለውን የድሃ ልጅ ልታስጨርሱ ስታስቡ በውኑ እንደትላንቱ እናንተ ልጆች በአውሮፓ እና በ አሜሪካ አስቀምጣችሁ ነው ወይስ አነሱም ከፊት አሉበት ?ለመሆኑ እናተ ጦርነት ብትጀምሩ በኢትዮጲያ ውስጥ ተበትነው ያሉት የትግራይ ልጆች ምን ሊገጥማቸው አንደሚችል አስባችሁታል ?ስለጦርነት ካነሳን ለመሆኑ የእናንተ ሰራዊት ከ ኢትዮጲያ ህዝብ ሰራዊት ጋር ሲነፃፀር ትልቅነቱ አስከምን ነው? ከትግራይ ህዝብ ውስጥ እናት ዘርፋችሁ ትከሻችሁ አስኪጎብጥ ተሸክማችሁ ሳለ የመጠጥ ውሃ እንኳን አጥቶ የሚቸገረው ድሃ የትግራይ ህዝብ ምን እያሰበ ነው ብላችሁ አስባችሁስ ታውቃላችሁ?የተከበራችሁ ህውሃት አባላት ዘሙኑስ 2011 ዓም መሆኑን እና እንደ 1967 ጫካ ስትገቡ እንዳልነበረበት ዘመን መሆኑንስ በባዶ ሆዳችሁ ጠዋት ስትነሱ ጭንቅላታችሁ ይህን ለማሰብ አድል አልሰጣችሁምን?በእውነቱ ለትግራይ ህዝብ ጠላት ማነው?ጠላት የገዛለትስ ማነው ?እናንተ አደለችሁምን? ።ኢትዮጲን ማተራመሳችሁ ሳያንስ የኤርትራ መንግስት ሊወጋን ነው።አማራ ሊወጋን ነው ።እንትና ሊወጉን እያላችሁ ህጻን ልጅ በአውሬ እንደሚያስፈራራ ወላጅ ሁሉን ማስፈራሪያ ስታደርጉ በውኑ የትግራይ ህዝብ የማያውቅ የማይረዳ ይመስለችኋልን?።

አስቲ ተመለከቱ እናንተ ከኢትዮጲያ ጫንቃ ላይ ስትረግፉ ሳውዝ ሱዳን ሰላም ሆነች።ሱማሌ ሰላም ሆነች ።ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን አለም ምን ይታዘብ ይመስላችኋል?ጦርነት ከፍቶ የመብራት ነው ፤የውሃ ነው፤ የስልክ ነው ወይስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ የምትሆኑት።ትላንት እና በህገ መንግስቱ ተደብቃችሁ ጠፍር ስትነቅሉ፤ስትገሉ፤ስትዘርፍ ፤የሃገርን ክብር አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ ስንት አስነዋሪ ተግባር ስተሰሩ፤ዛሬ ድግሞ ወንጀለኞችን ደብቃችሁ አስቀምጣችሁ ከፌደራል መንግስት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ስትገቡ ያልታያችሁ ህገ መንግስት ዛሬ ምነው ደርሶ ተቆርቋሪ ለመሆን ዳዳችሁ።ነው ወይስ ህግ መሆኑ ትዝ ያላችሁ ዶ/ር አብይ እጅ ላይ ሲደርስ ነው ?አዝማሪ እንደ እናንተ አይነት ሰው ኤኢቶ ግራ ቢገባው እንዲህ አለ “ፍየሊቷን አርዶ በጊቷን ደገማት፣ አንዲህ ሙልጭ አርጎ ይበላል ወይ አሳት”አለ ይባላል ።

እና ሃገር ፋብሪካ የሰራት ደፍተር አደለችም።እናንተ እንደምታስቡት በአንዴም ተቀዳ አታልቅም።እንደውም ቢሆን ኖሮ እናንተ ስልጣን ላይ በነበራችሁ ግዜ የልፋታችሁን ልኩን ታዩት ነበር። እንዋጋ ብትሉም የምትዋጉት ከገዛ ወንድሞቻችሁ ጋር ነው ።ያ ማለት እናት አለን የምትሉትን ወንድነት ከገበያ ሸምቶ ከሚያመጣው ጋር ሳይሆን እንደ እናንተው ኢትዮጲያውያን ጋር ነው ።ደግሞስ ከጦርነቱ በኋላ ምን መሆን አሰባችሁ?።ለስንት ግዜስ ልትዋጉ ነው ?ሌላውስ አለም ዝም ብሎ የሚመለከታችሁ ይመስላችኋል?የየሃገራቱ ዲፕሎማት ነጋ አልነጋ ብሎ ኢትዮጲያ ሲመላለስ ምን እየታሰበ ይመስላችኋል? በስተመጨረሻስ ከገባችሁበት እየገባ አንጠልጥሎ ለፍርድ እንደማያቀርባችሁ ማን አይዞአችሁ አላችሁ ?ልብ በሉ ኢትዮጲያ ውስጥ ትግራይ ህዝብን ጨምሮ በእናንተ ያልቆሰለ የለም ።ምን አልባትም አንድ ጥይት አስከምትተኩሱ ሊሆን ይችላል እየጠበቀ ያለው ።

ልብ በሉ ማንኛውም የምታደርጉት ተግባር አስከዛሬ ባልታየ ሁኔታ በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ የትግራይ ልጆችን ዋጋ ያስከፍላል ። እርግጥ ነው ስለነሱ አይመለከታችሁም ።ሁሉም ነገር እናንተን አስከጠቀመ ድረስ ብቻ ነው ።ያ ባይሆን በደርግ ያስፈጃችሁአቸው ልጆች ሳያሳዝኑአችሁ ዛሬም ለእናንተ ሰርዶ መጋጥ አፈር ሆነው ማብቀል እንዳለባቸው ማመናችሁ ምን ያህል እንደ ሰባችሁ እና ጥጋብ መቅኖ ያሳጣችሁ ብትሆኑም እንኳን ቅሉ ሌላው ኢትዮጲያዊ ግን ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና የሚሉ የትግራይ ወገኖቹን እየተጎዱ መሆኑን ሁሉም ይረዳል። አሁንም ደግሜ እላለሁ ወንድነት አንድ እግርን ውጭ አድርጎ አንዱን ውስጥ አድርጎ አደለም ።ወንድነት በሁለት እግር ፊት ለፊት ቆሞ ነው ።ይህ ማለት ለዚህ ጦርነት ሚስቶቻችሁ እና ልጆቻችሁ ከየአሉበት ሰብስባችሁ በማስልጠን ጦርነት ህመሙን ከሌላው ማህጸን በተወለደ ልጅ አደለም የምትፈትሹበት ።እናንተም ገብታችሁበት ነው ።

በተረፈ በትውልድ መሃል የሚኖር ከዳተኛ እና አጥፊ ህሊናው ወደ በረሃነት የተቀየረበት ብኩን ሰው ነው ።ማንቱም ስንኩል በመንገዱም ውድቀትን የዘረጋ ነው ።የፈርኦን ፖለቲካን መከተል እንደ ኤርትራ ባህር የሰፋ አበሳ ውስጥ ሰጥሞ ለመቅረት ነው እና አስቡበት።የሚመክራችሁ ሰው እንዳይኖር ሁሉም ትልቅ ይሆን ዘንዳ አንዳይቻለው ጥቅም በተባለ ሰንሰለት ጠርንፋችሁታል እና የምክር አድል አላገኛችሁም ።ስለዚህ ምክር በማጣት በርሃ ውስጥ ናችሁ። እና ወዮ ወዮታ አለብን ማለት በእውነት ደግ ነገር ነው ።ነገንም እድል ይሰጣል ።ከዛሬው የጦርንት ድቤ እና ማስፈራራት ይልቅ ትላንት አድል ነበራችሁ።መላው ኢትዮጲያ ፤መላው አለም በ እናንተ እጅ እና ከ እናንተ ጋር ነበር።ስለዚህ ትላንት አንደዘበት ከተነነ ዛሬ በምትፈጥሩት ጉም ዝናብ እናገኛለን ብላችሁ ከሆነ ይህ ስህተት አደለም ።ይህ ሰውነት ያላለፈበት ባዶነት የፈጠረው እኔነት ውጤት ነው ።
ይቆየን።

Share.

About Author

Leave A Reply