መርሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሶስት አፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ዛሬ ይጀምሯሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሶስት አፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ዛሬ በሰኔጋል ይጀምሯሉ፡፡

መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በሴኔጋል በመጀመር ሶስት የአፍሪካ አገራትን ለመጎብኘት ነው ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚያቀኑት፡፡

ጋና እና ናይጄሪያንም የሚሸፍነው ጉብኝታቸው ህገ ወጥ ስደትን መከላከል እና የምጣኔ ሀብት ትብብር ላይ እንደሚያተኩር ተመልክቷል፡፡

አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች እንደገለፁት አንዳንድ የአጉሪቱ ክፍሎች የሚያታየው አለመረጋጋቶች  በአውሮፓ ሕብረት አገራት ላይ የስደተኞች  ጫና እንዲያበረከት አድርጓል ᎓᎓

“በአፍሪካ ብዙ ግጭቶች ሲኖሩ አንዳንድ ሰዎች እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች እየሸሹ ነው” ብለዋል ቻንስለር አንጌላ ሜርክል᎓᎓

ሴኔጋል ፣ጋና እና ናይጄሪያ ከፍተኛ የሆኑ መሰናክሎች ያጋጥሟቸዋል እንዲሁም በአካባቢው በሚነሱ ግጭቶች ላይ መፍትሄ ለማግኘት ቁልፍ ሚና አላቸውም ብለዋል᎓᎓

ምንጭ፡‑ አልጀዚራ

Share.

About Author

Leave A Reply