መሰቦ ሲሚንቶ በምርቶቹ ላይ የ10 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከሚያዝያ 22 2010 ዓ.ም ጀምሮ በምርቶቹ ላይ በአማካይ የ10 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክብርአብ ተወልደ እንደገለፁት፥ የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ማስተካከያን ተከትሎ ፋብሪካው ከውጭ በሚያስገባቸው ከ45 በመቶ በላይ ጥሬ እቃዎችና ግብአቶች ላይ የ30 በመቶ ጭማሪ በመከሰቱ ነው የዋጋ ማስተካከያው የተደረገው።

የዋጋ ጭማሪው ከምርት አቅርቦት እጥረት ጋር አይያያዝም ያሉት ዋና ስራ አስከያጁ፥ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ በቀን እስከ 206 ቶን ሲሚንቶ በማምረት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የኦፒሲ፣ ፒፒሲ እና ፒ ኤል ሲ ምርቶች ላይ መሆኑን ገልጸው፥ የኦፒሲ ምርት ቀደም ሲል ሲሸጥበት ከነበረ 265 ብር በኩንታል ወደ 275 ብር ከፍ ብሏል።

በተጨማሪም የፒፒሲ ምርት ከ190 ብር ወደ 209 ብር በኩንታል፣ በፒ ኤል ሲ ምርት ላይ ደግሞ ቀደም ሲል ይሸጥ ከነበረበት 165 ብር በኩንታል ወደ 205 ብር ከፍ ማለቱን ፋብሪካው አስታውቋል።

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት አምስት አይነት የሲሚንቶ ምርቶችን እያመረተ እንደሚገኝና በቂ የምርት ክምችት እንዳለውም ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ምንጭ፤ ፋና

Share.

About Author

Leave A Reply