መንግስት ቀጥረን ወይም ተከራይተን እናስመጣ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮጵያ መንግስት ትቅጠር ወይም ትከራይ!

….. ንዝንዝ፣ ጭቅጭቅ፣ ወሬ… ከዛሬ ነገ አንድ ተስፋ ይዘን ወደ ተሻለ ነገር እንሄዳለን ስንል ተመልሰን ወደ ኋላ እንንደረደራለን።….. አሮጌውን ሸኘን ስንል አዲሱ ወዲያው ያረጅብናል።….

መቶሚሊየን ህዝብና ዘጠና ብሄር ሁሉም መንግስት ካልሆንኩ እያለ ሀገሪቱ በጩኸት ትተራመሳለች። ከአምስት አመት በላይ በተቃውሞና በስራ ማቆም አድማ ስትታመስ የኖረች ሀገር የህዝቦቿ በልቶ ማደር ሳያሳስበው ዛሬም የህዝቦቿን ሰላም የሚነሳ አጀንዳ ይፈለፈላል፣ ሌላ ንዝንዝ ……

ኢትዮጵያ ፖለቲካ መስራትና ሀገር መምራት ከባድ ራስ ምታት ሆኖባታል።…..ጭላንጭሎቿን ወደ ሙሉ ብርሀን ለመመለስ በሚጣጣር ጥቂት ቡድን ዙሪያ አፉን አሞጥሙጦ ‘እፍ ብሎ ለማጥፋት የተሰበሰበ የሀገር ሸህም በዝቷል።….

ሁሉም እሱ መሪ ካልሆነ፣ የሱ ቡድን ሀሳብ ካላሸነፈ፣ የኔ የሚለውን ካላሳተፈ መንግስትን ጠልፎ ከመጣል ሀገርን ከማፈራረስ አይመለስም።

ስለዚህ መፍትሄው አንድ ብቻ ነው።…እኛ እኛ ለጊዜው አልሆነልንም። ለመጨቃጨቅ፣ ለመነታረክና ለመናከስ የተፈጠርን ስለሆንን አንድ የጋራ ነገር ማግኘት አልቻልንም። በመሆኑም መንግስት እንከራይ!

አንድ መንግስት ተከራይተን ወይም ቀጥረን እኛ ወደ ቀን ስራችን ተመልሰን ኑራችንን መኖር እንጀምር።…

የራሱ ሙሉ ፓርላማ ያለው፣ ሚዲያ ያለው፣ ፖሊስ ወይም የጸጥታ አባላት ያሉት፣ ዴሞክራሲ ያለው መንግስት እንቅጠር…እኛ ጭቅጭቃችንን አቁመን ዝም ብለን ጠዋት ወደ ስራ ማታ ወደ ቤተሰብ፣ ቅዳሜና እሁድ ወደየ መዝናኛችን እየሄድን እንደ ሰው እንኑር። ሰው እንሁን።

ማቆሚያ የሌለው የፖለቲካ ጭቅጭቅ የሰውን ልጅ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰቡንም ይበላል። ያደክማል! ለውጥ ለሌለው ነገር በአተካራ ዘመን መፍጀት ኪሳራ ነው። ሰው ስንት አመት ይጨቃጨቃል? ስንት ዘመን ይከስራል? ….ጭቅጭቅ በራሱ ከመጠን ሲያልፍ ይጨንቃል!

ስለዚህ ፖለቲካውን የሚይዝልን መንግስት ተከራይተን ወይም ቀጥረን እኛ ህዝብ ሆነን እንኑር!

Share.

About Author

Leave A Reply