መንግስት በንግድ ውስጥ ተሳታፊ መሆኑን እንደሚቀጥል ተናገረ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

መንግስት በቅርብ አመታት ውስጥ መንገዱን እንደማያቆም የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ትላንት በሸራተን አዲስ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት ባለሀብቶቹ መንግስት መነገዱን ለእኛ ይተውልን ከንግድ እጁን ይሰብስብ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩን ጠይቀዋል ፡፡

ዶክተር ዐብይ አህመድ ሲመልሱም መንግስት በንግድ ውስጥ እጁን አያስገባ የሚለው ሀሳብ በቅርብ ጊዜ አይሆንም እንደዛ አትጠብቁ ብለዋቸዋል፡፡

መንግስት እየመረጠ ይነግድ ከሆነ ግን ትክክል ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በንግድ ውስጥ ቢሰማራም እጁን እያወጣባቸው የሚገኙ ዘርፎች አሉ ሲሉም የቡናና የባንክ ዘርፎችን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡

ምናልባት በሚቀጥሉት ሃያ አመታት መንግስት ከንግድ ሙሉ ለሙሉ አይወጣም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሻለው መንግስትም ባለሀብቶችም የሚችል የሚችሉትን ቢሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትላንቱ ለባለሀብቶች ጋር ባደረጉት ውይይትና የትውውቅ መድረክ ወቅት ስለ ውጭ ምንዛሪ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ መንገዶች አንዱ የሆነው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት የሚላኩት ገንዘብ ሲሆን አንዳንድ በመንግስት ላይ ያኮረፉ ግለሰቦች ግን ገንዘቡ እንዳይላክ ይከላከላሉ ያኔ ግን የሚጎዳው መንግስት ሳይሆን ደሃው ዜጋ ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህም መንግስት የሚቀጣበት ትክክለኛ ቅጣት አይደል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በጣም ቅርቡ የሹማምንት ሹም ሽር እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር በተያያዘ ከሀገር ገንዘብ እየዘረፉ በውጭ አገር የሚያስቀምጡ በተለይ የመንግስት ባለስልጣናትን ገንዘብ ማስመለሳችን አይቀርም ሲሉም የቻይናን አሰራር ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡

 

Share.

About Author

Leave A Reply