መንግስት ከኦ.ዲ.ኤፍ ጋር መወያየቱን ይፋ አደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኦሮሞ ደሞክራቲክ ግንቦር /ኦዴፍ/ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑ በመንግስት ተቀባይነት አገኘ

አሰላለፉን ከኦነግ የለየውና የኦሮሞ ደሞክራቲክ ግንቦር /ኦዴፍ/በሚል ስያሜ ራሱን በመጥራት የሚንቀሳቀሰው ግንባር ከመንግስት የቀረበለትን ጥሪ አክብሮ ህገ መንግስቱን በማክበር በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑ ከከፍተኛ አድናቆት ጋር ተቀባይነት ማግኝቱን መንግስት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ጋር ባካሄዱት ውይይትና ድርድር ነው ድርጅቱ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ የወሰነው፡፡

አጠቃላይ ውይይቱ የተሳካ ጥሩ አገራዊ መንፈስና መግባባት የሰፈነበት ነበር ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ከግንባሩ ጋር ስለተካሄደው ውይይትና ድርድር በላከው መግለጫ፡፡

ሃገርና ህዝብን ባስቀደመ እና በሰለጠነ መንገድ የሚያደረግ ውይይት እና ድርድር፣ የሃገራችን ጉዳይ ያገባናል፣ሰላማዊ በሆነ መስመር መታገልም ውጤታማ ያደረጋል ብለው ከሚያምኑ አካላት ጋር በቀጣይም ውይይትና ድርድር ለማድረግ መንግስት በፅኑ ይፈልጋል ለተግባራዊነቱም አበክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

የኦዴፍ ከፍተኛ አመራሮችም በቅርብ ቀናት አዲስ አበባ እንዲገቡም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ቀሪዎቹ ውይይቶችም እዚህ አዲስ አበባ እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡

ለወደፊቱም ህገ መንግስቱን ባከበረና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በአገራችው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ከሚፈልጉ አካላት ጋር ለመወያየትና ለመደራደር መንግስት ዝግጁ መሆኑን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ባለከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኢቲቪ

Share.

About Author

Leave A Reply