ሙስና እና የገንዘብ ችግሩን ለመፍታት ሁለት ፖሊሲዎች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +
  1. የብር ቅየራ (demonetization)

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ cash economy ነዉ፡፡የገንዘብ ዝዉዉር ባንክን ወይም ቴክኖሎጅን በመጠቀም አይደርግም፡፡ነጋዴዉ ታክስ የመክፈል ባህል የለዉም፡፡ በዛ ላይ የንግዱ ዘርፍ በትቂት ግሩፖች የተያዘ ነዉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰወች በቢሊየን የሚቆጠር የኢትዮጵያ ብር በኬሻ፤ፍራሽ ዉስጥ፤ ጣሪያ ዉስጥ ቤታቸዉ ዉስጥ ይደብቃሉ፡፡ በጎረቤት ሀገራት ለምሳሌ በሱዳን፤ ጅቡቲ፤ ሶማሊያ እና ኬንያ በቢሊየኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ብር ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ shadow economy ወይም Black money የምንለዉ ነዉ፡፡ ነጋዴዎች፤ የመከላከያ ሰወች፤ደህንነቶች፤ ደላሎች እና ባለስልጣኖች አንደኛ በባንኮች ዉስጥ ይሄን ያህል ብር ማስቀመጥ የማይፈልጉት የት መጣ የሚል ጥያቄ ይነሳል ተብሎ ነዉ፡፡ ሁለተኛ ልያዝ እችላለዉ በሚል ነዉ፡፡ ሶስተኛ ህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ስለሆነ ታክስ ላለመክፈል ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት በ ቢሊየኖች ብር ገደማ እንደዚሁ ህብረተሰቡን ሊጠቅም በማይችል ሁኔታ ይዘዋወራል ማለት ነዉ፡፡ ይህ ትልቁ የሙስና መንገድ ነዉ፡፡ ስለዚህም መንግስት ባልታሰበ ጊዜ የ 50 እና የ 100 ብረ ኖቶችን በአዲስ መልክ በመቀየር ሌቦች እቤቱ ዉስጥ እና በጓሮ የተቀበረዉን በቢሊየን የሚቆጠር አሮጌዉን ብር ወደ ባንክ አምጥቶ በአዲሱ እንዲቀይር ማድረግ ነዉ፡፡ ይህን ፖሊሲ የሚተገበር ከሆነ ለማንም ሳይነገር በአሳቻ ሰአት የሚደረግ ይሆናል፡፡

ገንዘቡ ሲቀየር ለምሳሌ ከ 100 ሺህ ብር በላይ ለመቀየር ይዞ የመጣዉን ሰዉ ያን ያህል ገንዘብ ታክስ ተከፍሎበት እንደነበር፤ እንዴት ቤት ዉስጥ ተከማችቶ እንደተቀመጠ እና ከየት እንደተገኘ የታክስ ባለሙያወች ያጣራሉ፡፡ ካልሆነ ይወረሳል ወይም 300 እና 400 % ታክስ ይጣልበታል፡፡ ይህ ጥቁር ገቢያ ዉስጥ ያለዉን ገንዘብ ወደ ፋይናንስ ሴክተሩ ያስገባዋል፡፡ የባንክ saving ያድጋል፡፡ ይህ በመሆኑ በትቂት ሰወች በሙስና ምክንያት የተደበቀዉ ገንዘብ ወደ ህብረተሰቡ ይመጣል ማለት ነዉ:: ይህን በማድረግ የባንክ ሰርቪሱን በየጎጡ በማስፋት cashless economy መገንባት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ዉጭ ሃገር የተከማቸ ዶላር ላይ ብቻ ሳይሆን አገር ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ብርም አለ፡፡

  1. Financial council (ከፖሊሲ አነስ ያለ ምናልባትም ስትራቴጅ)

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ክራይስስ ዉስጥ ነች፡፡ ይህ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወይም በብሄራዊ ባንክ ገዥ ብቻ በሚሰጥ የፖሊሲ አቅጣጫ የሚጠገን አይደለም፡፡ ሰለዚህም ከዩኒቨርስቲ፤ ከግል ባንኮች፤ ከመንግስት ሰወች፤ ከብሄራዊ ባንክ፤ ከገንዘብ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከለሌለሎቸች ተቋሞች የተወጣጣ ካዉንስል በማቋቋም የሀገሪቱን የገንዘብ ፖሊሲ ይመረምራል፤ የዉጭ ምንዛሬ ጉዳይ ያጠናል፤ unemployment rate ፤ ኢንፍሌሽን፤ GDP እና የመሳሰሉትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመተንበይ ለማክሮ ኢኮኖሚዉ የፖሊሲ ግበአት በማዘጋጀት የመንግስት ሰወችን እና የግሉን ሴክተር ማማከር ይችላል፡፡ በማክሮነና ማይክሮ ኢኮኖሚክስ ፣ public finance, public Policy, monitory economics, strategic public fiancé and Trade በመሳሰሉት ዙሪያ እዉቅና ያላቸዉን ባለሙያወች ማሰባሰብ፡፡ ይሄ የወደቀ ኢኮኖሚ በነደሚቱ ማማከር የሚመለስ አይደለም፡፡

(ሚኪ አማራ)

Share.

About Author

Leave A Reply