ማሳሰቢያ ለወሎ ህዝብ (ከመንግስቱ ዘገየ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ባለፉት አመታት ካንድ ክልል አካባቢ ተደራጅተው ወደ ወሎ በሚንቀሳቀሱ የወንበዴዎች ቡድን ከፍተኛ ዝርፊያና ግድያ ሲፈጸም እያየን ነው ። እነዚህ የወንበዴ ቡድኖች ከጀርባቸው የማይታዩ የጠላት እጆች እንደሚያግዟቸው መገመት አያዳግትም ። እንደፈለጉ ይዘርፋሉ ፤ ይገድላሉ ፤ ሩጠው ወደ መንደራቸው ሄደው ይደበቃሉ ።

እነዚህ ወንበዴዎች በተለይ በወልዲያና ደሴ ኮምቦልቻ ወዘተ በተለየ ሁናቴ በመደራጀት በውንብድና እየተንቀሳቀሱ ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎችን ጭምር እየፈጸሙ መሆናቸውን ተገንዝበናል ። ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከውጭ ታሳድራለች እንደሚባለው እስከዛሬ ጌቶቻቸውን ተማምነው የተደራረበ ግፍ ሲፈጽሙብን ከርመዋል ።

አሁን ግን መክት አማራ ብለናል ። ሰሞኑን ደሴ ከተማ ዘግናኝና ጭካኔ የሞላበት የግፍ ግድያ የፈጸሙት የወንበዴ ቡድን አባላት በፖሊስ ያልተቆጠበ ጥበብና ትጋት በቁጥጥር ስር ውለዋል ። ግድያ መፈጸማቸውንም ከነ ድርጊታቸው ሙሉ ዝርዝር አምነዋል ።

በእውነት እነዚህ ግፈኞች የፈጸሙት በደል የኢትዮጲያዊነትን መተዛዘንና ርህራሄ ከስሩ ነቅሎ የጣለ የአራዊት ተግባር የተቀላቀለበት ፍጹም ዘግናኝ ጭካኔ ነው ። የደሴ ከተማ ፖሊስ የወንበዴውን ቡድን በህግ ስር እንዲውል ማድረጉ የሚያስመሰግነው ተግባር ቢሆንም አሁንም በመላው የወሎ ግዛት የሚኖረው ማህበረሰብ በቀጣይነት አካባቢውን ከተደራጁ ያንድ ጎጥ ወንበዴዎች ራሱን በንቃት እንዲጠብቅና እንዲመክት አብዝቼ አሳስባለሁ ።
ጉድ ነው እኮ ። ካገሪቱ ባንክ የሚዘርፉት አንሶ ደግሞ ቤት ለቤት መጡብን?

Share.

About Author

Leave A Reply