ማነው አዛዡ? ማነው ታዛዡ?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከነገ በስቲያ ከሃምሳ ሁለት ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ እንደሚያከፋፍል የአዲስ አበባ መስተዳደር የሰጠውን መግለጫ አስመልቶ ጃዋር መሀመድ “ቤቶቹ የተሠሩት ከፊንፊኔ ድንበር ውጭ ስለኾነ ቅድሚያ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ መስተዳድር ሳይወያዩበት ለማከፋፈል እንዳትጣደፉ!” ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ይህን ማሳሰቢያውን የተመለከቱ ብዙዎች ”የዚህች ሀገር መንግስትና መመሪያ ሰጭ ማነው?”እስከማለት ድረስ ግራ በተጋቡበት ወቅት እነ ጃዋር የመንግስት ሰዎችን በጫናና በማስፈራሪያ መጠምዘዙን ቀጥለዋል።

እንደምንታዘው በጅምር ለውጡ ላይ እንቅፋትና ጥርጣሬ እያሳደሩ ከሚገኙት አበይት ነገሮች አንዱ በአንዳንድ የኦሮሞ አክቲቪስቶችና ገና ባልጠራው የኦዴፓ መዋቅር ውስጥ የሚስተዋለው “የተረኝነት” ስሜት ነው።

ከወራት በፊት የጣይቱ ሐውልት በአዲስ አበባ እንዲቆም በመስተዳድሩ የተወሰነው ውሳኔ ጃዋር ባሰማራቸው “የጋዜጠኛ ፖሊሶች” መታገዱ ይታወሳል። ሌሎችም ተመሳሳይ አይነት የጎንዮሽ ትዕዛዝ መሰል ማሳሰቢያዎችን ተከትለው የሚወሰዱ እርምጃዎንም እየተመለከትን ነው።

ለመሆኑ የከንቲባ ታከለ ኡማ አስተዳደር ከነገ በስቲያ ሃምሳ ሁለት ሺህ ቤቶችን በዕጣ እንደሚያከፋፍል ያሳለፈውን ውሳኔ የጃዋርን ትዕዛዝ በመፍራት ያስቀረው ይሆን? ወይስ ውሳኔውን ይተገብረዋል? ወሳኙ ማን እንደኾነ ከነገ በስቲያ አብረን እናያለን።

(መንግስቱ ሀ/ማርያም)

 

Share.

About Author

Leave A Reply