“ማዶላ” የተሰኘው መፅሐፍ እንዲቃጠል መደረጉ እንዳስደሰታቸው የጋሞ ብሔረሰብ ተወላጆች ተናገሩ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የጋሞ ብሔረሰብ ለረዥም ዘመናት ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመተሳሰብ፣ በመቻቻልና በመፈቃቀር የኖረ መሆኑን የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች ይህንን አኩሪ ዕሴት የሚያጎድፍ ብሎም ብሔረሰቡን የማይወክል ፍፁም የተሳሳተ ይዘት ያለው እና ህገ-መንግስቱን የሚፃረር መፅሀፍ ተፅፎ ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ የብሔረሰቡ ተወላጆች ድርጊቱን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲያወግዙና የመፅሐፉ ፀሐፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ሲያሳስቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ምንም እንኳን ውሳኔው የዘገየ ቢሆንም በቀን ሰኔ 19/2010 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ ተዘዋዋሪ ችሎት መፅሐፉ ሕገ-ወጥ እንደሆነ ወስኖ እንዲቃጠል ባስተላፈለው ትዕዛዝ መሰረት ተግባራዊ መደረጉ እንዳስደሰታኛው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የጋሞ ብሔረሰብ የፍቅርና የመቻቻል ተምሳሌትነቱን በተግባር በማሳየት ለዞኑ ልማትና አንድነት በጋራ እንሰራለን ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ስርዓት ለማስቀጠል የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

(የዞኑ ኮሚኒኬሺን ጽ/በት)

Share.

About Author

Leave A Reply