ምልአተ ጉባኤው: ለሲኖዶሳዊ ልዩነቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ዝግጁነቱን አረጋገጠ፤ አስተዳደራዊ ማሻሻያ በጥናት እንዲፈጸም አዘዘ፤ ነገ ጠዋት መግለጫ ይሰጣል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለዛሬ ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የጠራውን አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ በሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ሒደት እና በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ከተወያየ በኋላ ውሳኔና መመሪያ በመስጠት ማምሻውን አጠናቋል፡፡

ሲኖዶሳዊውን የዕርቀ ሰላም ሒደት በተመለከተ፡-

 • ልኡካን አባቶች፣ እንዳስፈላጊነቱ የሚወስኑበትን ሙሉ ሥልጣን ሰጠ፤
 • በሠየማቸው 3 ልኡካን አባቶች የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ወስኗል፤
 • ለቋሚ ሲኖዶሱ፣ የአካሔድና ሥርዐት 5 ነጥቦች፣ ይኹንታ ሰጥቷል፤
 • የሀገር ወስጥና የውጭ ሲኖዶስ መባሉ“ታሪካዊና አሳዛኝ ግድፈት ነው፤”
 • ሽማግሌዎች፣ሒደቱን የሚያስጨርስ ነገር ሊቀርብ እንደሚገባ መከሩ፤

 

 • “ከቅ/ሲኖዶስ ዕውቅናና ውክልና ውጭ የሚሰጡ መግለጫዎች አግባብነት የላቸውም፤”
 • “ዕርቀ ሰላሙ ሲደከምበት የኖረ እንጅ አኹን የተፈጠረ እንዳልኾነ መታወቅ አለበት፤”
 • “ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በ4 የተለያዩ ጊዜያት ልኡካን መድቦ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤”
 • “በ2ቱም በኩል የተላለፈው ውግዘትና ሌሎች ዝርዝሮች ከዕርቀ ሰላሙ በኋላ ይታያሉ፤”

 

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ወቅታዊ ችግሮችን በተመለከተ፣ 6 አባላት ያሉት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴ ያቀረበውን መነሻ ተመልክቶ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በዋናነት ተይዞ የሌሎች አህጉረ ስብከትም ዐበይት ክፍተቶች በጥናት ተደግፎ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አዝዟል፤

 • ትልቁ ችግር፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅም ማጣት ነው፤
 • አፋጣኝ እርምት ባለመሰጠቱ፣ ምእመናን እና ወጣቶች ቢሮዎችን አሽገዋል፤
 • “ሕዝባዊ መማክርት ለሲኖዶስ” ለሚሉ ክፍሎችም መንገድ ሊከፍት ችሏል፤
 • በባለሥልጣናት ንግግሮችና በተቋማት ሪፖርቶች ለክሥና ወቀሳ አጋልጦናል፤
 • ለሰብአዊ መብቶችመከበር ግንባር ቀደም ከመኾን ይልቅ በጥሰት ተጠቅሳለች፤

 

 • በመንግሥት ከተለዩ 18 ጥሰቶች 2ቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ብቻ ተገልጸዋል፤
 • የአ/አበባ ሀ/ስብከትና የአጥቢያ ሓላፊዎች የተደራጀ ዝርፊያ ዐይነተኛው ነው፤
 • ሀገረ ስብከቱን፣ ለ4 ሊቃነ ጳጳሳት የመክፈል የከሸፈ ሐሳብ ውድቅ ተደርጓል፤
 • የአ/አ እና የሌሎችም አህጉረ ስብከት ክፍተት የሚታይበት ልዩ ጥናት ያሻል፤
 • የተጠናው የመዋቅር ለውጥም፣ሙስናና ጎጠኝነት የምናጠፋበት ነውና ቢታይ፤
 • ከሃይማኖት ሕጸጽ እና ሌብነት ነጻ የኾኑ የታገዱ ሠራተኞች እየታዩ ይመለሱ፤

 

በተያያዘ ነገ በሚያወጣው መግለጫ፡-

 • ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላምና ትብብር መመለሳቸውን ቅ/ሲኖዶሱ አንሥቷል፤
 • ቀጣይነቱ የሠመረ እንዲኾን ግንኙነቱን በመደገፍ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል፤
 • የጠ/ሚኒስትሩ፣“የመደመር እሳቤ” በመግለጫ ረቂቁ ቢነሣም በማከራከሩ ቀርቷል፤

Share.

About Author

Leave A Reply