ምንም ያልተነገረለት የኩሱሜዎች ጭፍጨፋ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኩሱሜ ብሔረሰብ አናሳ ብሔር በመሆናቸው ብቻ በደቡብ ክልል መንግስትና በድራሼ ወረዳ ጥምር ጦር ከ 3 ሳምንት በፊት ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም በተከፈተባቸው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አክረናቸው ዛሬም የት እንዳለ ያልታወቁትን ጨምሮ በአንድ ቀን ብቻ ከ 30 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ከ 21 በላይ አስክረን ተሰብስቦ፤ 8 አስክረን በእሳት ተቃጥሎ፤ ሙሉ መኖሪያቸውና ንብረታቸው ወድሞ፤ የተረፈው ተዘርፎ በመኪና ወደ ድራሼ ተጭኖ ሙሉ ብሔረሰቡ ዛሬም ፍትህ አጥቶ በመዳ ላይ ተበትኖ እየተሰቃዬ አንድም የመንግስት አካል፣ አንድም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ፣ አንድም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሚዲያ ሳይዘግብ እስከ ዛሬ ታፍነ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ነው።

የኩሱሜ ህዝብ የጠቅላይ ሚንስቴር ቢሮን ጨምሮ ጉዳዮ ለሚመለከታቸው ሁሉም የመንግስት አካላት እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ዘግናኝ ግፍ ማውገዝ አለበት እንላለን!

ህዝቡ ከሰነድና ከምስል እስከ ቪዲዮ በቂ መረጃ አሰባስቧል! ዛሬ ላይ ብታፈን ነገ አደባባይ መውጣቱ አይቀርም!

ፍትህ ለኩሱሜ ህዝብ!
ኤሊያስ መሰረት

Share.

About Author

Leave A Reply