Thursday, January 17

ምክር ለአብን መሪ ሊቀመንበር ደስአለኝ ጫኔ – የብሄርተኞች ሁሉ እናት አንድ ናትና ብሄርተኝነትህን መገንባት ስትፈልግ ሌላ የትም አትሂድ!ወንድምህን ጃዋርን ተከተል!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(ብዙዎች እየመከሩህ ነው…. በሳል ምክር አትቀበል:: ያ ዋጋ የለውምና:: ..በዚያ የብሄርተኞች እናት አይኑን አስራ የተወችው ፈረስ አለ…. የበኩር ወንድምህ ጃዋር የጋለበው…. ተስቦ ከማያውቀው ልጉዋም የተቁዋጠረ መልእክት ታገኛለህ:: ጃዋር የተናዘዘው ነው…. እርሱ ሄዶበት ተጠቅሞበታል…. በእርግጥ ትጠቀምበታለህ…. እያንዳንዱዋ መልእክት ምንም ሃሰት ያልተጨመረባት ናት…”መዳረሻውን መንገዱ አይገምግም” ይላል ፈረንጅ…. “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ይላል ሃበሻ…. ያ ነው መንገዱ )

1, ተግዳሮቴ ያልከውን እያነክ እምትጥለበትን ሸምቀቆህን ምረጥ… እስከምትፈልገው ግፋ… ለልብህ ያሰኝህን ተናገር…. ሃሳብህን የማይቀበል የሚሞግትህንም ሁሉ ኦሮሞ-ፎቢክ (ዛሬ በነአብይና ለማ መምጣት እርቃኑን የቀረ ዋጋቢስ ክስ) ብለህ አሸማቅ:: ከሌሎች የሚወሰልትን ሃሳብህን የሚጻረር ወገንህንም ጎበና በተባለ ስሙ ማሳፈሪያ እንዲሆን አባቶቼ በሰሩት ስርአት እዘልፋለሁ…. ጩህ! “ኡ!.. ኡ!…እንዴት ነው ከኦሮሞ-ፎቢክ ጋር የሚኖረው??!” ብለህ አልቅስ…. ሩብ አለምህ አብሮ ያለቅሳል

2, በሃሰት ክሰስ! ኢሳትን “የአማራ ጣቢያ ነው” ብዬ ለፍፌአለሁ…. የኢትዮጽያ ብሄርተኛ ነን የሚሉትን ሁሉ እንዲህ ያለ ፖለቲካ የለም ለማለት “የአማራ ፖለቲካ” ብዬ አስተምሬአለሁ::… እንዳልሆነ ልቤ ቢያውቅም… እንዲያ ነውና ብሄርተኝነት ቤትዋን የምትሰራው…. ኢሳት “ጸረ-ኦሮሞ ነው” በል…. በዚያ ትርፉ ብዙ ነውና… ከሃሰት ከቶስ ምን ትጎዳለህ ?

3, ቴዲ አፍሮን አሳድጄዋለሁ…. “የሚኒሊክ ጦርነት ቅዱስ ጦርነት” ነው አለ ብዬ አድማ አስመትቼበታለሁ:: ውሸት እንደሆነ የመጽሄቱ አዘጋጅ ሁሉ እንዳረጋገጠው አውቃለሁ… ብሶት አሰባስቤበታለሁና ጠቅሞኛል:: “በቁስላችን እንጨት ሰደደ” ብዬ ህዝቡን ሆድ አስብሼዋለሁ:: በትግስት ገሜ በኩል “ቴዲ አፍሮ ግጥም ከህጻናትና በረንዳ አዳሪዎች ዱቤ እየወሰደ ሳንቲም ይከለክላቸዋል ወይንም የማይረባ ሂሳብ ይሰጣቸዋል” ብዬ ሳላፍር አጽፌበታለሁ… አውቃለሁ ሃሰት ነው… ግን ይሉኝታ አያስፈልግም…. የሰውየው ስብእና እንዲላሽቅ ሞክሬአለው… ህዝቡን አነሳስቼበት የዘፈን ድግሱ እንዳይካሄድ አስደርጌበታለሁ… ፍጹም ውሸት ጥሩ ነው::

4, ከዚህ ነው የመጣችሁት… ስደተኞች ናችሁ በል… ሲርቅ ወላ ከአረብ! ወላ ከአንታርክቲካ! ነው የመጣችሁት በል:: ሲቀርብ የሚኒሊክ ሰፋሪዎች በል…. እውነትና ሃሰት አይደለም ቁም ነገሩ… ውጥረት መፍጠር… ወዳጅህን መሰብሰብህ ነው ጉዳዩ:: “ሺህ አመት አብረን ኖረናል አንለያይም” የምትልበት አውድ ሲፈጠር ትለዋለህ…. ችግር የለም:: ወደሁዋላ ሄዶ ነገር የሚሰልቅ የለም…. እንዲረሱ የተፈጠሩ ናቸውና…. ዛሬ መናገር ያለብህን ዙሪያህን እስካሰባሰበና እስካስደሰተ ተናገረው:: ከማዳጋስካር ይበል ከሊቢያ በለው…… እኛ እዚሁ ነው የበቀልነው በል….እስከ ግዮን መዳረሻ እኛ ከዚህ በቅለናል….አስብል…

(***…ጸሃፊው በዚህ ድጥ ተጎትቶ መግባቱን በሃዘን ያስታውሳል…. እንዴት ያለ አስቀያሚና የውሸት “ፖለቲካ” ነው ይላል ለራሱ !!.)

5, ነገሩን አሳምረው ማንም ገልብጦ የሚያይ የለምና:: ሁሌም ቅዱስ ነኝ: ሁሌም ርጉም ነህ በል አስብል… እንደ በረሃ ንብ መንጋ ዘመድ ይከብሃል . ከሰሜን የተነሳ ሚኒሊክ ወረረኝ 10 ሚሊየን ጨረሰ ብለህ አስለቅስ….. በዛው አፍህ ጎንደር ቤተመንግስት በ16ኛው ዘመን ጦር ነበረን በል… አንተ እዛ አበባ እየጎዘጎዝክ ደረስክ ወይ? ብለው ቢያሾፉ ነው:: እስካሁን በተቃራኒው የቆመ እዬዬ አላየሁምና

6,አዎ ብያለው… መባል ነበረበት… መነጣጠል መገነጣጠል እንዲሁ በስጋ ጉዳይ ብቻ አይበቃም… እያንዳንዱ ገመድ መበጣጠሱን ማረጋገጥ… እናም ብያለው
“አንድም ኦሮሞ አማራ ቤተክርስቲያን ሄዶ እንዳያስቀድስ” ብያለው… “የራስህን ቸርች ሰርተህ ብቻህን አምልክ” ብያለሁ.. ወገን ነብሱ ሁሉ ከጎኔ ነበር

7, ይህ በቂ አይደለም:: በበቀል አነሳሳ…. ክርስቲያኑን በሜንጫ እንጨርሳን በል…. ያስፈራል ግን በል…. ምክኒያት አይጠፋም…. አንዱ ኦሮሞ-ፎቢያ: ነው..ይከልልሃል:: ከዚያ ተቆራርጦ ቀርቦብኝ ነው ምናምን ብለህ ትዋሻለህ…ኦሮሞ-ፎቢያ በተባለ ሴንጢ ታሳቅቀዋለህ

8, ድርቅ በል… ፊንፊኔ በል… ነዋሪዎችዋንም የሚኒሊክ ርዝራዥ ብያለው… ከፊቴ የሚቆሙትንም ግልገል ነፍጠኛ ብዬ ተሳድቤአለሁ….ፖለቲካቸውን ቤት አልባ ብያለሁ:: ጠቅሞኛልና አይጸጽተኝም… መዳረሻህን በሂደቱ ገምግም (the means justifies the end) የሚል የሞራል አስተምህሮ ፌክ ነው… ይህ ብሄርተኝነት ነው…. አሁንም ያው ነው… አዲስ አበባ መሬቱ የኦሮሞ ህዝቡ የአማራ ነው ብያለሁ…. አማራ ክልል ሄጄ “በአዲስ አበባ ላይ ስልጣን ከሆነ ሁለታችን ከፍተኛ ሼር አለን ሽግር የብለይ” ብያለው…. ምን ተፈጠረ?…. ወለሃንቲ !!

9, ኢትዮጽያዊ ነን የሚሉ ሌሎችን ህዝቦች የባርነት ስነ ልቦና ያልራቃቸው አስብያለሁ… በግርማ ጉተማ በኩል “የሽሮ ሜዳ ነዋሪዎች ሃይለስላሴ ከደቡብ ዶርዜ ሃገር በባርነት ያመጡዋቸው ናቸውና ዛሬም የባርነት ስነልቦና አላቸው” የሚል አሰቃቂ ስድብ አስልኬያለሁ…

10, ወደፊት ግፋ… ማንም የሁዋላውን አያይብህም:: ፈረንጅ “ነጻ ምሳ የለም” ይላል:: ለሁሉም ሂሳብህን ትከፍላለህና ነው…. እንግዲህ ሆን ብዬ ለተናገርኩት: በሌሎች ላይ ላመጣሁት ኪሳራ ‘ኢሪስፖንሲብል’ ብሎ ግዜ ጠብቆ ጉዴን የሚያወጣ የለምና …በአፋቸው ነውር ወጥቶ ከማያውቁት ፖለቲከኞች እኩል እጠራለሁ….. ምክኒያቱም ቤቴን ሰርቻለሁና

(ታምራት)

Share.

About Author

Leave A Reply