ምክር ቤቱ በመጪው ሰኞ ስራውን ይጀምራል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመኑን መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም ይጀምራል፡፡ ምክር ቤቱ ስራውን የሚጀምረው ሰኞ ከሰዓት በኋላ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ በሚያደርጉትም የመክፈቻ ንግግር መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

የመክፈቻው ንግግር የ2010 ዓ.ም በጀት ዓመት የመንግስት ዋና ዋና የስራ እንቅስቃሴዎችንና ውጤቶችን፤ ዋና ዋና ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮችን፤ በበጀት ዓመቱ በምክር ቤቱ ህግ እንዲወጣላቸው የታሰቡ ጉዳዮችን እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ይይዛል፡፡

በተጨማሪ የመክፈቻ ንግግሩ በበጀት ዓመቱ ውስጥ መንግስታዊ አካላት ስለሚያከናውኑት ተግባራት አቅጣጫ ከማስቀመጥ ባሻገር ለህዝቡም ስለመንግስት ውጥኖች መረጃም የሚሰጥ ጭምር መሆኑን ተነግሯል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply