ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሹመትን አፀደቀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ሹመትን አፀደቀ።

በዚህ መሰረትም ዶ/ር ጣሰው ገብሬ የኮሚሽኑ ከሚሽነር እንዲሁም ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሹመትንም አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፤ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ በማድርግ ማጽደቁን ሪፖርተራችን ይመር አደም ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።።

Share.

About Author

Leave A Reply